የቤተ ክርስቲያን ታራክ።
<< ቀዳሚ
ቀጣዩ >>
William Branham.የቤተ ክርስቲያንዘመን መልእክትን ሙሉ በሙሉ እንድትረዱት የመልእክተኞቹን ስም፤ የዘመናቱን ርዝመት ሌሎች ተካተው ያሉ ጉዳዮችን ማወቅ እንድችልየረዱኝን ልዩ ልዩ ቀኖናዎች ወይም መመሪያዎች ለማብራራት እወዳለሁ።
የእያንዳንዱዘመን መልእክተኛ ማን እንደሆነ ለመለየት ከጌታ የተሰጠኝ ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ነው። በእውነታውም ከሆነ የመጽሐፍቅዱስ የመሠረት ድንጋይ ነው። የማይለዋወጥ ከእግዚአብሔር ያገኘሁት መገለጥነው የእርሱም አካሔዶች እንደማይለዋወጡ ሁሉ ዕብራዊያን13፡8 እንዲህ ይላል “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።”
ይሄው እዚህጋር፡ የማይለዋወጠው አምላክ በማይለዋወጠው መንገዱ መጀመሪያ ላይ ያደረገው ነገር እስከ መጨረሻው ድረስ እስኪከናወን መቀጠልአለበት። መቀያየር የሚባል ነገር የለም።
አሁንበመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቃሉ ላይ የሰፈረውን የመጀመሪያይቱ ወይም የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደተመሠረተች እናእግዚአብሔር እንደተገለጠባት በትክክል ማወቅ ችለናል።
ቃሉ አይቀየርም ወይም ሊቀያየር አይችልም ምክንያቱም ቃሉ እግዚአብሔር ነውና።ዮሐንስ1፡1, “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
ስለዚህበባለ ሐምሳው ቀን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን መለኪያችን ነች። ያ ነው ንድፉ ሌላ ንድፍ የለምምሁራኖች ኃጢአት ምንም ይበሉምንም ያንን ንድፍ እግዚአብሔር አልቀየረውም። እግዚአብሔር በባለሐምሳ ቀን ያደረገውን በየአብያተ ክርስቲያናት ዘመናቱ ሁሉማድረጉን ይቀጥላል።
ክ... የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን።
እስያ የተቀመጡት።
የኤፌሶን።
የኤፌሶንከተማ በእስያ ከነበሩ ሶስት ታላላቅ ከተማዎች መካከል አንዱ ነበረ። ከቀዳሚዋ ኢየሩሳሌም ከሁለተኛዋ ከአንጾኪያ ቀጥሎየክርስትና እምነት ሶስተኛ ከተማ ተብላ ትጠራለች ገዢውሮም ነበር ቃንቃው ግን ግሪክ ነበር እጅግ ባለጸጋከተማ ነበረች የታሪክአጥኚዎች እንዲያምኑት ዮሐንስ፤ ማርያም፤ ጴጥሮስ፤ እንድርያስ እና ፊሊጶስ ሁሉም የተቀበሩት በዚች ውብ ከተማ ነበር።
ክ... የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን።
የሰምርኔስ።
የሰምርኔስ ከተማ በኤፌሶን በሰተ ሰሜን በኩል የሰምርኔስ የባህረ ሰላጤ ጫፍ ላይ የምትገኝ ነች። የረቀቀ ባህር ወደብ ያላት በመሆኑ ምክንያት የንግድ ቦታ ነበረች ወደ ውጭ በመላክ የታወቀች ናት። የንግግር ጽሑፍ መማሪያዎች፤ ፍልስፍና፤ ሕክምና፤ ሳይንስ እና የሕንጻ ጥበብ ትምህርቶች ያላት በመሆኑ በዚህም ትለያለች።
ሰምርኔስ የሚለው ቃል ሚርከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “መራራ” ማለት ነው። በድን እንዳይበሰብስ የሚያደርግ መድሐኒት አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። በዚህ ዘመን ስም ላይ ሁለት አይነት ትርጉም እናገኝበታለን በሞት የተሞላ መራራ ዘመን።
ክ... የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ዘመን።
የጴርጋሞንም።
ጴርጋሞን (የጥንት ስም) ሚሲያ በተባለ ስፍራ በሶስት ወንዞች የውኃ መንገድ ያላትበአንደኛውም አማካኝነት ከባህር ጋር የሚያገናኛት ሆና የተቋቋመች ናት። በኢስያ ታዋቂ የነበረች ከተማ ናት ከአሌክሳንድሪያቀጥሎ በባህል ቤተመጻሕፍትነት የምትታወቅ ነች ሆኖም ግን በቤተመቅደስ ውስጥም በሕይወት ያለ እባብ እየተቀለበ በማምለክየሚታወቁ ኤስኩላፐስ የሚባሉ ሕይወት ያለውን እባብ አምላኪዎች እንዲያመልኩ በነጻነት የተፈቅደላቸው ታላቅ የኃጢአት ከተማነበረች።
የሰይጣን ዙፋን እና መኖሪያ ስፍራ። ጴርጋሞስ(ከሰው ዘር አመጣጥ ጋር በተያያዘ) የመጀመሪያው የሰይጣን መኖሪያ ስፍራ አልነበረችም በቀጥታም ሆነ በታሪክ ባቢሎን የሰይጣንዋና መቀመጫ ስፍራ ነች የሰይጣናዊ አምልኮ መነሻ በባቢሎን ነበር።
የትያጥሮን።
በታሪክ ስንመለከተው የቲያጥሮን ከተማ በራእይ መጽሐፍ ላይ ከተገለጹት ሰባቱ ከተማዎች አነስተኝ ከተማ ስትሆን ሚሲያ እና አይኦኒያ በተባሉ ክልሎች አካባቢ የተቀመጠች ነች እንዲሁም በተለያዩ አልቅቶች በተሞሉ ወንዞች ተከብባለች። ሸክላ ሰሪዎች፤ቆዳ ፋቂዎች፤ ሸማኔዎች፤ አቅላሚዎች፤ልብስ ሰፊዎች … የመሳሳሉት ማኅበራት ያሉባት በመሆኑ የተነሳ ጥሩ የፋይናንስ ገቢ የሚገኝባት እንደሆነች ትታወቃለች። የፐርፕል ሻጭ የነበረችው ሊድያ በአውሮፓ ውስጥ በጳውሎስ አማካኝነት ከተቀየሩ ቀደምት አማኞች ከነበሩት መካከል አንዷ ነች።
ይህችን ከተማ መንፈሳዊ ጥቆማን እንደያዘች እንደ አራተኛዋ ዘመን ቤተ ክርስቲያን አድርጎ መንፈስ የመረጠበት ምክንያት በነበራት የሃይማኖት እንቅስቃሴ ነበር። በዋናነት የትያጥራን ዋና ሃይማኖት የነበረው የአፖሎ ታይሪሜኖስ አምልኮ ነው ንጉሥ ነገሥቱን እንደ ጣዖት ከማምለክ ጋር ተያይዞ አፖሎ የፀሐይ አምላክ በመሆን ተሰይሞ እና ከአባቱ ቀጥሎ ወደ ሥልጣን የመጣው ዚዩስ.
የትያጥሮን የሚለው ስም ትርጉሙ “የሴቶች የበላይነት.”
ክ... የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን።
የሰርዴስ።
ሰርዴስ የጥንቷ የልድያ ዋና ከተማ ነበረች። ከሊድያን ነገሥታት እጅ ወደ ፋርስ ከዚያም ወደ ታላቁ እስክንድር ተላለፈ። በታላቁ አንጾኪያ ተጣለ። የሮማ ነገስታት በዚያን ጊዜ እስከተቆናጠጡበት ጊዜ ድረስ ግዛቱ በጴርጋሞን ስር ነበር። በጢባርዮስ ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥና ቸነፈር ባድማ ሆናለች። ዛሬ የፍርስራሽ ክምር እና ሰው የማይኖርበት ሆኗል።
የዚህች ከተማ ሃይማኖት ሲቤሌ የተባለችው እንስት አምላክ ንጹሕ አምልኮ ነበር። የቤተ መቅደሱ ብዛት ያላቸው ፍርስራሾች አሁንም ይታያሉ።
ክ... የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ዘመን።
የፊላደልፊያ።
ፊላደልፊያ ከሰርዲስበስተደቡብ ምስራቅ ሰባ አምስት ማይሎች ትገኛለች። በልድያ ውስጥ ሁለተኛው ትልቁ ከተማ ነበረች። ታዋቂ በሆነ የወይን ጠጅ በሚያበቅልወረዳ ውስጥ የተገነባች ነች። በበርካታ ኮረብታዎች ላይ ተገንብቷል። ሳንቲሞቻቸው የቦካከስን ጭንቅላትና የባካኩትን (የባችከስቄስ) ምስል ይዘዋል።
ከተማዋ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጦች ብትሰቃዩም የጊዜ ቆይታዋ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ከተገለጹት ከተማዎችረዘም ያለ ነው። በእርግጥ ከተማዋ በአሁኑ ጊዜ አላሴር ወይም በእግዚአብሔር ከተማ በቱርክ ስም ስር ትገኛለች።
የሎዶቂያ።
“ሎዶቅያ” የሚለውስም “የሰዎች መብት” ማለት ሲሆን በጣም የተለመደ ነበር እናም በዚህ ስያሜ የተሰየሙትን ንጉሣዊ ሴቶችን በማክበር ለበርካታ ከተሞች ተሰጥቷል። ይህች ከተማ በትንሹ እስያ ውስጥ በፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና ገንዘብ ነክ ከሆኑት ከተሞች አንዷ ነች። ታዋቂ የሆኑ ዜጎች በርካታ ንብረቶች ለከተማይቱ ተወስደዋል።
የታላቁ የሕክምና ትምህርት ቤት መቀመጫ ነበር። ሕዝቡ በኪነ ጥበብ እና በሳይንስ የሚታወቁ ነበር። ለሃያ አምስት ሌሎች ከተሞች የካውንቲ መቀመጫ እንደ መሆኑ ብዙውን ጊዜ ‹ከተማ› ተብሎ ይጠራ ነበር። እዚያ የጣዖት አምልኮ የሆነው ዜኡስ ነበር። በእርግጥ ይህች ከተማ በአንድ ወቅት ለአምላካቸው ክብር ዲዮፖሊስ (የዙስ ከተማ) ተብላ ትጠራ ነበር። በአራተኛው ምዕተ-ዓመት አንድ አስፈላጊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተደረገ። በተደጋጋሚ ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ሙሉ በሙሉ ከተማው እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል።
ክ... የሎዶቂያ ቤተክርስቲያን ዘመን።