የፍጥሞ ራዕይ።
ዮሐንስ በፍጥሞ።
William Branham.ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የፍጥሞ ራዕይ።ራእይ 1:9-10,
“እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራዉንና መንግስቱን የምካፈል ዮሐንስስለ እግዚአብሔር ቃል እና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ፡፡
በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ በኃላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ትላቅ ድምጽሰማሁ.”ይሄ ተከታታይየኢየሱስ ክርስቶስ በአካል መገለጥ ራዕይ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ተባሮ ለተጓዘዉ ለዮሐንስ የተሰጠ ነዉ፡፡ ይህች ትንሽ ደሴትበታችኛዉ እስያ በኤግያን ባህር ሰላሳ ማይል እርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ቋጥኝማ አካባቢ እና በእባቦች፤በእንሽላሊት፤ እናበጊንጥ የተወረረ ስፍራ ነዉ፡፡ በተወሰነ መልኩም የንግድ ቦታ ነዉ፡፡ የሮማ መንግስትም እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ወንጀለኞች እናየፖለቲካ እስረኞችን ለመቅጣት የሚጠቀምበት ቦታ ነዉ፡፡
ካስተዋላችሁትዮሀንስ እራሱን ለቅዱሳኑ ያለበትን ሁኔታ ሲገልጽ የመከራዉ ተካፋይ ወንድማችሁ በማለት ነዉ፡፡ የቀደምት ቤተ ክርስቲያን በዚህጊዜ በመከራ ዉስጥ ስታለፍ የነበረችበት ጊዜ ነበር፡፡ እምነታቸዉ “በየቦታዉ መጠላቱ” ብቻ ሳይሆን ሁሉምሰዎች እራሳቸዉ በእስር ያሉና የሚገደሉ ነበሩ፡፡ ዮሐንስም እንደ ብዙሃኑ ሰዎች ለእግዚአብሄር ቃል እና ለኢየሱስ ክርስቶስምስክርነት በእስር እየተሰቃየ ነበር፡፡ በታሰረ ሰዓት እሱን ለመግደል ብለዉ በፈላ ዘይት ዉስጥ ለሃያ አራት ሰዓት ከተዉትበከንቱ ደከሙ ስለሆነም በጣም የተናደዱት ወታደሮች ጠንቋይ ነዉ ብለዉ ወደ ፍጥሞ ደሴት እንዲሔድ አደረጉት እግዚአብሔር ግንከእሱ ጋር ነበረ ነገር ግን ከዛ ደሴት ተርፎ እስከ ህይወቱ ፍጻሜ ድረስ በእረኝነት ወደ አገለገለበት ወደ ኤፌሶን ተመለሰ፡፡
በሰባቱ ማህደር ዉስጥ ያለዉ የአካሉ ክብር፡፡
ራእይ 1:14-16,
“ራሱና የራስ ጠጉርም እንደ ነጭ የበግ ጠጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ ዓይኖቹም እንደእሳት ነበልባል ነበሩ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር ድምጹም እንደ ብዙ ዉኃዎች ድምጽ ነበረ በቀኝ እጁምሰባት ከዋክብት ነበሩት ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ጸሐይ ነበረ፡፡”ኢየሱስለዮሐንስ የቀረበበት መንገድ በጥልቀት የሚያንቀሳቅስ እና የሚያነቃቃ መልኩ ነበር፡፡ ስለ ቃሉ ሲል በስደት ዉስጥ ለነበረዉእነሆ አሁን ህያዉ የሆነዉ ቃል በፊቱ ቆመ፡፡ እያንዳንዱ የተገለጸበት መገለጫዎች ሁሉ የየራሳቸዉ ትርጉም ያላቸዉ ሆኖ በብርሃንየታየ ራእይ፡፡ እንዴት ያለ የከበረዉ ማንነቱ መገለጥ ነዉ፡፡
1. ጸጉሩ እንደ በረዶ ነጭ ነዉ፡፡
ዮሐንስ በመጀመሪያ ያስተዋለዉ እና የገለጸዉ ነገር የጸጉሩን ነጭ መሆን ነበር፡፡ነጭ እና እንደ በረዶ የበራ ነበር ይህ ከእድሜዉ እርጅና የተነሳ አይደለም በፍጹም አይደለም፡፡ የደመቀ ነጭ መሆኑየሚያመላክተዉ የእድሜዉን ጉዳይ ሳይሆን ልምዱን፤ ብስለቱን እና ጠቢብነቱን ነዉ፡፡ ዘላለማዊ የሆነዉ እድሜ የለዉምለእግዚአብሔር ጊዜ ምኑ ነዉ? ጊዜማለት ለእግዚአብሔር ትንሽነት ማለት ነዉ ነገር ግን ጥበብ ማለት ንጉስ ሰለሞን እግዚአብሔርን የእስራኤልን ህዝብ የሚፈርድበትንጥበብ እንደጠየቀዉ ትልቅነትን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ምድርን ሁሉ የሚዳኝ እርሱ አሁን እየመጣ ነዉ፡፡
ይሄዉ እዚጋዳንኤል በዛ በነጭ ጸጉሩ ተመለከተዉ፡፡ መጽሐፍቶቹን የሚገልጥ እና የሚፈርዳቸዉ ዳኛ ነዉ፡፡ ዳንኤል በደመና ዉስጥ ሲመጣተመለከተዉ ዮሐንስም በትክክል ያየዉ እንዲህ ነበር ሁለቱም በተመሳሳይ መልኩ ተመለከቱት፡፡ ሁለቱም በዳኛዉ ትከሻ ላይ የፍርድመቀነት ተመለከቱ፡፡ ንጹህ እና ቅዱስ ሆኖ በሙሉ ጥበብ አለምንበጽድቅ ለመዳኛት የሚገባዉ ሆኖ ቆሞ አዩት፡፡ ሀሌሉያ፡፡
2. የእሱ ዓይኖች እንደ እሳት፡፡
አይኑ እንደ እሳት በደንብ አስቡት እነዛ በሃዘን እና በእንባደብዝዘዉ የነበሩት አይኖቹ እነዛ በአላዛር መቃብር በርህራሄ ያነቡት አይኖቹ ከሀዘን የተነሳ ነፍሰ ገዳዮቹን መመልከት ተስኗቸዉ የነበሩ “ይቅር በላቸዉ” ብሎ የነበሩት እነዛ አይኖቹ አሁን የእሳት ፍምሆነዉ የተቃወሙትን ሁሉ መልሶ የሚከስበት የዳኛ አይኖች ናቸዉ፡፡ እንደ ሰዉተገልጦ በነበረ ሰዓት ሁሉም ሰዉ ካላቸዉ ስሜቶች በብዛት ከገለጻቸዉ ስሜቶች መሃል ሁልጊዜ ያለቅስ ነበር ነገር ግን ከነዛለቅሶዎች በስተጀርባ እርሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ እነዚሁአይኖች ራእይን ተመለከቱ የጠለቀዉን የሰዎችን ልብ ይመለከታሉ ሀሳባቸዉን ያነብባሉ ልዩ ልዩ አካሄዳቸዉንም ያዉቃሉ እነዛየተቃጠሉት በስባሽ አይኖች የእግዚአብሔር ነበሩ፡፡ የእሱን ማንነት ያዉቁ ለነበሩት ያለቀሰዉ “…እኔእንደሆንሁ ባታምኑ በኃጥያታችሁ ትሞታላችሁና፡፡”
ዮሐንስ 8፡24,
“እኔ የአባቴን ስራ ባላደርግ አትመኑኝ ባደርገዉ(የአባቴን ስራ) ግን እኔን ስንካ ባታምኑ ስራዉን እመኑ፡፡”
ዮሀንስ 10፡37-38 እንደ ብሉይኪዳኑ ኤርሚያስ አልቃሻ ነብይ ነበርሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል አይቀበሉም ነበርና መገለጡን ቸል ይሉ ነበርና፡፡እነዛ ነበልባል የመሰሉ የዳኛዉ አይኖች በአሁንሰአት እንኳን የሁሉንም ስጋ ለባሾች ህይወት እየመዘገቡ ናቸዉ፡፡ በምድር ላይ ከአንዱ ወደ ሌላዉ ቦታ እየተዘዋወረ፡፡የማያዉቀዉ አንዳች ነገር የለም የልብን ፍላጎት እና እያንዳንዱ የሚያስበዉን ሁሉ ያዉቃል ያልተገለጠ አንዳች ነገር የለምየምናደርጋቸዉ ነገሮች ሁሉ በፊቱ የተራቆቱ ናቸዉ፡፡ እስኪ አስቡት በአሁን ሰዓት እንኳን እናንተ የምታስቡትንያዉቃል፡፡
አዎ ዳኛዉ ፍርድን ለመስጠት በነበልባል አይኖች ቆማል፡፡ የምህረት ቀናቶች አብቅቷል፡፡ኦ፡ ያ ሰዉ ጊዜ ሳለ ንስሀ መግባት እና በጽድቅ ፊቱን መፈለግ ይችል ነበር፡፡ አለም በእሳት ከመፍረሷ በፊት መንተራሻዉንእቅፉ ዉስጥ ያደርጉ ነበር፡፡
3. እግሩ እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፡፡
“እግሩም እንደ ነጠረ የጋለ ናስ ይመስል ነበረ” ናስ የሚታወቀዉበአስደናቂ ጥንካሬዉ ነዉ፡፡ በመቀጥቀጥ የሚጠነክር እንደ ናስያለ አንዳች ነገር እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ይሄ እግሩን ለመግለጽ የተጠቀመበት ናስ ግን ይበልጥ አስደናቂ ነዉ እንደ ነጠረ የጋለናስ ስለሆነ ማንም ያላለፈበትን ያለፈ ጣእም ስላለዉ፡፡ ያም ትክክል ነዉ፡፡ ናስ የመለኮታዊ ፍርድን ያመላክታል፡፡ እግዚአብሔርየሚያዉጀዉ እና የሚያሳልፈዉ ፍርድ፡፡
ዘሁልቁ 21፡8-9,
“ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።
ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።” እስራኤላዊያን ሀጥያትን ሰሩ ሐጥያት ፍርድን ማግኘት አለበት ስለዚህእግዚአብሔር ሙሴን በመስቀያ ላይ ከናስ የተሰራ እባብ በዓላማ ላይ እንዲሰቀል አዘዘዉ እናም ማንም ቀናብሎ የተመለከተዉ ሁሉ ከሀጥያት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡ነገር ግን አንድ ቀን እነዛ የናስ እግሮች በምድርላይ ይቆማሉ እናም በእኩልነትና በፍጹምነት በምድር ሁሉ ላይ ፈራጅ ይሆናል፡፡ ማንም ከዛ ፍርድ የሚያመልጥ አይኖርም ፍትህአይቀለበስም ማንም የሚቆጣ አይኖርም ጻድቅ ያልሆነ ሁሉ ሳይጸድቅ ይቀራል፡፡ እድፋሙም እድፋም ይሆናል ስለዚ የማይቀየረዉ እርሱአይቀየርም ተቀይሮም አያዉቅ ወደፊትም አይቀየርም እነዛ የናስ እግሮች ጠላቶቹን ይደመስሳቸዋል፡፡ ሀሰተኛዉ ክርስቶስ ፤አዉሬዉ፤እና ምስሉ እንዲሁም በፊቱ መጥፎ የሆነዉ ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ ስሙን አበላሽቶ በማንጸባረቅ እና ከሐሰተኛዉ ክርስቶስ ጋርበመጨፍለቅ ስሙን ያስጠፉትን የቤተክርስቲያን ስርአት ያጠፋቸዋል፡፡ አመጸኞች፤እግዚአብሔር የለም ባዮች ፤ ከህይወት በኃላ ሌላ ህይወት የለም ባዮች፤ዘመናዊያኖች፤ነጻ ነን ባዮች ሁሉምበዛ ይገኛሉ፡፡ ሞት፤ሲኦልእና መቃብር ሁሉ በዛ ይገኛሉ፡፡ አዎ ይገኛሉ፡፡ እሱ ሲመጣ መጽሃፍት ሁሉ ይገለጣልና፡፡ በዛን ሰአትነዉ ለብ ያለችዉ ቤተክርስቲያን እና አምስቱ ሞኞች ደናግላን የሚገኙት፡፡ እርሱ በጉን ከፍየሉ ይለየዋል፡፡ሲመጣ መንግስትን ሁሉይረከባል፡፡ መንግስት የእርሱ ነዉና ከእርሱም ጋር ሺ ጊዜ አስርሺዎች እና እርሱን ለማገልገል የምትመጣዉ ሙሽራይቱ ትገኛለች፡፡ክብር! ኦ አሁን ካልሆነ ሌላ ጊዜ የለም ከመርፈዱ በፊት ንስሃ ግቡ ከሙታኖች መካከል አምልጡና በመንፈሱ እንዲሞላችሁእግዚአብሔርን ፈልጉት ካልሆነ ግን ዘላለማዊ ህይወትን ታጣላችሁ ጊዜ ሳለ አሁን አድርጉት፡፡
4. ድምጹ እንደብዙ ወኆች ድምጽ ይመስላል።
አሁን ዉሃ ምንን ነዉ የሚወክለዉ ራእይ 17፡15 ላይ አንብቡት “...ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችምናቸው።” ድምጹ ብዙ ህዝቦች እንደሚናገሩ ይመስላል ይሄ ምንድን ነዉ? ይህ ፍርድ ነዉ፡፡እነዛ ድምጾች በዘመናት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ክርስቶስን የመሰከሩ እና ወንጌልን የሰበኩ የብዙ ምስክሮች ድምጾች ናቸዉና፡፡ እነዛ ድምጾች ማስጠንቀቂያዎችንአልሰማ ላሉ ሀጥያተኞች ላይ ለፍርድ የሚነሱ የሰዎች ድምጾች ናቸዉ፡፡ የሰባቱ መልእከተኞች ድምጽ ከፍ ብሎ እና በግልጽይደመጣል እነዛ ታማኝ ሰባኪዎች የኢየሱስን አዳኝነት ሀይል የሰበኩ፤የዉሃን ጥምቀት በኢየሱስ ስም ነዉ ብለዉ የሰበኩ ፤የመንፈስ ቅዱስን ሀይል እና መሞላት የሰበኩ፤ ከራሳቸዉ ህይወት ጋር ሳይሆን ከቃሉ ጋር የተጣበቁ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስአማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስ ድምጾች ነበሩ፡፡ ዮሐንስ 17፡20 “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም”
ኦ፡ ማየት ከቻላችሁ አለምን ያጠፋዉ ዉሃ ነዉ ነገር ግን ኖህን እና ቤተሰቦቹን መላ ምድርንለኖህ ማዳን የቻለዉ ያ እራሱ ዉሃ ነበር፡፡ ድምጹን ስሙት ለንስሀ እና ለህይወት የሚጣራዉን የአገልጋዮቹን ድምጽ ስሙት፡፡
5. በቀኝ እጁ ላይ ያሉ ሰባት ከዋክብት፡፡
“በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ነበሩ” አሁን በርግጥ ከቁጥር ሃያ ላይ የሰባቱ ከዋክብት ሚስጥር እነማን እንደሆኑአዉቀናል፡፡“እናም የሰባቱ ከዋክብት ሚስጥር ለሰባቱ አብያተክርስቲያናት የተላኩ ሰባቱ መላእክቶች(መልእክተኞች)ናቸዉ፡፡” አሁን እርሱእራሱ ለእኛ እስከተረጎመልን ድረስ በምንም መንገድ እዚጋ አንሳሳትም፡፡ እነዚህ ሰባት ከዋክብት ለሰባቱ ተከታታይየአብያተክርስቲያናት ዘመን የሚላኩ መልእክተኞች ናቸዉ፡፡ ከኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ አንስቶ አሁን እስካለንበትየሎዶቂያ ዘመን ያለዉ መልእክተኛ ድረስ ለህዙቡ እዉነተኛ መልእክት አምጥተዋል፡፡ ስማቸዉ በርግጥ አልተጠቀሰም፡፡ ለእያንዳንዱዘመን አንድ መልእክተኛ ሆኖ ሰባት ተብለዉ ብቻ ነዉ የተቀመጡት፡፡ ለነበሩበት ለዛ ዘመን የእግዚአብሔርን ቃል በመጠበቅ ለህዝቡእዉነተኛ መልእክትን አምጥተዋል፡፡ ለእያንዳንዱ አንድ አንድ በመሆን፡፡ ለእዉነተኛዉ ብርሃን በታማኝነት ጸንተዉ የቆሙ ነበሩ እያንዳኑዱዘመን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ ሲሉ ያ መልእክተኛ ያንን ዘመን ወደ ቃሉ ይመልስ ነበር፡፡ ጥንካሬያቸዉን ያገኙት ከጌታ ነዉ ባይሆንኖሮ ግን ያንን ሁሉ ማዕበል አይችሉትም ነበር፡፡ ብዙም እሩቅ አይደለም አንድ ሰዉ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ባመነችበት በመቆሟ እናሳትቀያየር እያደገች በመሆኗ እዉነተኛ ልትባል ትችላለች አለኝ፡፡ ፈጽሞ በዛ መልክ አይደለም የትኛዉም ቤተክርስቲያን መንግስትከበስተጀርባዉ ሆኖለት ከቃሉ ያልሆነ የራሱ ባህል ኖሮት እና ዲያብሎስን ሊያነሳሳ የሚችል አንዳችም የአገልግሎት መገለጫዎችሳይኖረዉ በርግጥም መቀጠል ይችላል፡፡ ያ መለያዉ አይደለም፡፡ ነገር ግን እነዛ አነስተኛ ህብረቶች አባሎቻቸዉ የበታች ሆነዉከሚታዩበት ፤ ለአንበሶች ለሚሰጡበት፤ ለሚሰደዱ፤ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ለሚንገላቱ እንደዛም ሆኖ ለቃሉ ታማኝ ለሆኑ ያሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ነዉ የእምነታቸዉን ጦርነት እንዴት እንዳሸነፉ እና እንደጸኑ ስታስቡ ያ ተአምር ነዉ፡፡
እናም ይሄ መጽናናት ለሰባቱ አብያተክርስትያናት ዘመን መልእክተኞች ብቻ አይደለም በእግዚአብሔር ያለ እያንዳንዱእዉነተኛ አማኝ ከእርሱ ፍቅርን እና ሃይልን ማግኘት ከእግዚአብሔር የሆነዉን ጥቅም ሁሉ መቀበል የአማኞች ሁሉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔርለመልእክተኞቹ የሰጠዉ ሁሉ ለሁሉም አማኞች ተምሳሌት ነዉ መልካምነቱን እና ተንከባካቢነቱን ለሚያምኑ የአካሉ አባሎች ሁሉምነዉ፡፡
6. በሁለት አፍየተሳለ ሰይፍ።
“ከአፉ ሁለት አፍ ያለዉ ሰይፍ ይወጣል” እብራዊያን 4፡12 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥የሚሰራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ሁለት አፍያለዉ ሰይፍ ይወጣል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነዉ፡፡
አሁን ጳዉሎስ ቃሉም ሆነ ድምጹ በሀይል የተገለጠነዉ አለ፡፡ የተሰበከዉ ቃል እራሱን በተግባር አሳይቷል፡፡ ልክ እንደ አመጸኛ የሚቆራርጥ ሰይፍ ወደ ሰዉ ጥልቅ ሀሳብ ይገባልልክ እንደ ቀዶ ጠጋኝ ቢላ በሽታዎችን ሁሉ ይቆራርጣል እናም ከእስራት ነጻ ያወጣል፡፡ የቀደምት አማኞች በሄዱበት ስፍራ ሁሉወንጌልን(ቃሉን) ለመስበክ ይሄዳሉ የተነገረዉንም ቃል እግዚአብሔር በምልክቶች ያጸናላቸዋል፡፡ በሽተኞች ይፈወሳሉ፤አጋንንት ይወጣል፤በአዲስቋንቋ ይናገራሉ፡፡ ያ ቃሉ በተግባር ሲገለጥ ነዉ፡፡ ያ ቃል አማኝ በሆኑ ክርስቲያኖች አንደበት ሳይሰራ ቀርቶ አያዉቅም፡፡በዚህ በመጨረሻዉ ዘመንም ባለች እዉነተኛ የቃል ሙሽሪት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ በጠነከረና በታልቅ ሁኔታ እየሆነ ነዉ፡፡ኦ፡እናንተ ትንሽ መንጋ፤ እናንተ ታናናሾች በቃሉ ላይ ጽኑ በአንደበታችሁም በልባችሁም ሙሉት እናም አንድ ቀን እግዚአብሔርመንግስትን ይሰጣችኃል፡፡
7. ፊቱ እንደፀሐይ ያበራል።
በራእይ 21፡23 ላይ,
“ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር። አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤” ይሄ አዲሲቱእየሩሳሌም ነዉ በጉ በከተማይቱ ይሆናል ከእርሱ መገኘት የተነሳ ሌላ ብርሀን አያስፈልጋትም በዛ ጸሐይ መዉጣትና መግባትአያስፈልጋትም እራሱ ጸሐይ እና ብርሃን ነዉና ወደ ዛ የሚገባዉ ህዝብ በእርሱ ብርሃን ይመላለሳል ያ ቀን ከፊታችን በመሆኑአትደሰቱምን? ዮሐንስ ያንን ቀን መምጣት አይቶታል አዎ ጌታኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!ት.ሚልኪያስ4፡1-3,
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥
ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡”
ይሄዉ በድጋሚጸሀይ ባላት አቅም ሁሉ ታበራለች ኦ፡ የእግዚአብሔር ልጅ በሰባቱ መቅረዞች መካከል በታላቅ ሀይል ሲያንጸባርቅ ዳኛዉ በዚያሲቆም ስለ እኛ ሲል የተሰቃየዉ እና የሞተልን የአምላክን ቁጣ ፍርድ በላዩ ላይ ተቀበለ እንደ ናስ የጠጠረዉን የእግዚአብሔርንቁጣ የወይን መጭመቂያ ብቻዉን ወሰደዉ፡፡ ቀደም ሲል እንዳልነዉ የእርሱ ድምጽ ለሀጥያተኞች በአለት ዳርቻ ላይ እንዳለ የማእበልድምጽ የሚያስፈራ ነዉ ነገር ግን ለቅዱሳኑ የእርሱ ድምጽ ለእረፍት ጋደም ብለን በክርስቶስ ላይ ረክተን እንደምንሰማዉ የጅረትምልክት ነዉ ፡፡ ባላያችን ላይ እንደሚያሞቅ ጨረር ፍቅር እንዲህ ይለናል አትፍሩ እኔ ያለሁ፤የነበርሁ የሚመጣዉ ነኝ እኔ ሁሉንቻይ ነኝ ከእኔ በቀር ሌላ የለም እኔ አልፋ እና ኦሜጋ ነኝ ሁሉ በሁሉ ነኝ እርሱ የቆላ አበባ የንጋት ኮከብ ነዉ፡፡ አስርሺህእጥፍ ለነፍሴ እረፍት ነዉ፡፡ አዎ፡ ያ ታላቁ ቀን ሊመጣነዉ በክንፎቹ ጥላ ስር የጽድቅ ጸሐይ ከፈዉስ ጋር ትወጣለች፡፡ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ... የፍጥሞ ራዕይ።