ያች ሴት ኤልዛቤል።


  የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።

ያች ሴት ኤልዛቤል።


William Branham.

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን።

የዮሐንስ ራእይ 2:20-23,
20 ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤
21 ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።
22 እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤
23 ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።

ስለ ኤልዛቤል የተማርነው የመጀመሪያውና እጅግ አስፈላጊው ነገር የአብርሃም ሴት ልጅ አለመሆኗ ወይም እንደ ሞዓባዊቷ ሩት እንዳደረገችዉ ወደ እስራኤል ነገዶች ለመግባት የተሳተፈች አለመሆኗ ነው ፡፡ በፍጹም፡፡ ይህች ሴት ለሲዶን ቄስ የነበረው የ ‹ሲዶን› ንጉሥ የኤትባል ልጅ (1ኛ ነገሥት 16፡31) ነበረች፡፡ ከእርሱቀዳሚው የነበረዉን በመግደል ዙፋኑን አገኘ፡፡ ስለዚህ ወዲያውኑ የነፍሰ ገዳይ ሴት ልጅ መሆኗን እናያለን፡፡(ይህ በእርግጥ ቃየንን ያስታውሰናል፡፡)የእስራኤልምአካል የሆነችበት መንገድ እግዚአብሔር ለአህዛብ ተቀባይነትንያገኙ ዘንድ ባስቀመጠዉ መንፈሳዊ መንገድ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በአሥሩ የእስራኤል ነገዶች ንጉስ ከሆነዉ ከአክዓብጋር በመጋባት ነዉ። ቀደም ሲል እንዳየነው ይህ አንድነት መንፈሳዊ አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ነበር፡፡ እናም በጣዖት አምልኮ ውስጥ የተሳተፈችው ይህች ሴት የእውነተኛውን አንድአምላክ አምላኪ የመሆን ትንሽ ፍላጎት አልነበራትም፣ ይልቁንም እስራኤልን ከጌታ የማጥፋት ልባዊ ፍላጎት ጋር መጣች፡፡

እስራኤል(ዐሥሩ ነገዶች) የወርቅ ጥጃዎችን ማምለክ ምን እንደ ሆነ ቀድሞውኑም ያውቁ ነበር፣ ሆኖም ግን ለጣዖት የተሸጡ አልነበሩም ፣ ምክንያቱም አመለካቸውእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን እንዲሁም የሚከተሉትም የሙሴን ሕግ ብቻነበር፡፡ ነገር ግን አክዓብ ከኤልዛቤል ጋብቻ ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ጣዖት አምላኪነት በፍጥነትመገስገስ ጀመረ፡፡ ይህች ሴት ወደ አስታሮት(ቬነስ)እና በኣል(የፀሐይ አምላክ)ቤተመቅደሶች ውስጥ ካህን መሆንስተጀምር ነዉ እስራኤል የህይወት ቀውስ ዉስጥመግባት የጀመረዉ፡፡

ይህንን በአእምሯችን ይዘን አሁን በዚህ የትጥሮን ዘመን የእግዚአብሔር መንፈስ ምን እንዳስቀመጠ ማየት እንጀምራለን፡፡ እንዲህነዉ።
አሀዓብ ኤልዛቤልን አገባ እናም እርሱ መንግስቱን ለማጠንከር እና ደህንነቱን ለማረጋገጥ እንደ ፖለቲካዊ አቅጣጫ አሳይቷል፡፡ ቤተክርስቲያን በቆስጠንጢኖስ ስር ባገባች ጊዜ ያደረገችው ያ ነው፡፡ ምንም እንኳን መንፈሳዊ አየር ቢያስቀምጡም ሁለቱም በፖለቲካዊ ጉዳዮች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ አሁን ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን መሆኑን ማንም ሊያሳምነኝ አይችልም፡፡ እሱ ክርስቲያንየሆነ በመምሰል ክርስቲያኖችን አጥማጅ የሆነ አረማዊ ነበር፡፡ በወታደሮች ጋሻ ላይ ነጭ መስቀሎችን ቀለም ቀባ፡፡ እሱ የኮሎምበስ አመጣጥ ነበር። በቅዱሳን ሶፊያ አናት ላይ መስቀልን የማድረግባህልን አስጀመረ፡፡

ሁሉንም ሰው፣ አረማውያንን፣ ስመ ክርስትናን እና እውነተኛ ክርስቲያኖችን አንድ ላይ የማሰባሰብ ሀሳብ የቆስጠንጢኖስ ነበር፡፡ እና ለጊዜው ለእውነተኞቹ አማኞች ከቃሉ የጠፉትን ወደ ቃሉ ለመመለስ የሚሳካላቸው ይመስልነበር፡፡ ወደእውነት እነሱን ማምጣት እንደማይችሉ ሲመለከቱ፣ ከፖለቲካ አካሉ ለመልቀቅ ተገደዱ፡፡ ከዚያ በኋላ እነሱ መናፍቅ ተብለዉ ተሰደዱ፡፡

በአሁኑ ሰአትም ተመሳሳይ ነገር ነዉ እየሆነ ያለዉ ብዬ መናገር እችላለሁ፡፡ ሰዎቹ አንድ ላይ እየተሰበሰቡ ነው፡፡ አይሁዳዊ፣ ካቶሊክም ሆኑ ፕሮቴስታንቱም ለሁሉም ሰው የሚስማማ መጽሐፍ እየጻፉ ነው፡፡ የራሳቸው የኒቂያ ምክር ቤት አላቸው ግን ኢኩሚኒካል ምክር ቤት ብለው ይጠሩታል፡፡ እና እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የሚዋጉ ማን እንደሆኑ ታውቃለህ? እውነተኛውን ጴንጤቆስጤዎች ነዉ የሚዋጉት፡፡ ጴንጤቆስጤ የሚባል ድርጅት ማለቴ አይደለም፡፡ እኔ ማለቴ የጴንጠቆስጤ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ በመሆናቸው በመካከላቸው ምልክቶችና ስጦታዎች ስላሉት በእውነት መንገድ ማለፋቸዉን ማለቴ ነው፡፡

አሀዓብ በፖለቲካ ምክንያት ኤልዛቤል ባገባት ጊዜ የብኩርና መብቱን ሸጠ፡፡ ወዳጆቼ ሆይ ከድርጅቱ ጋር ከተቀላቀላችሁብታምኑም ባታምኑም ብኩርናችሁን ትሸጣላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የወጣው እና ከዚያ በኋላ የተመለሰው የፕሮቴስታንት ቡድን ሁሉ የብኩርና መብታቸውን ይሸጣል፣ እናም ብኩርናዎን ሲሸጡ ልክ እንደ ኤሳው ነዎት -ያለቅሳሉ ይፀጸታሉ፣ ግን ምንም የሚፈይደዉ ነገር አይኖርም፡፡ ማድረግ የሚችሉት አንድ ነገር ብቻ ነው፣ ይኸውም፣ “ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከሏ ውጡ እና የኃጢያቷ ተካፋይአትሁኑ!” እኔ ትክክል ያልሆንኩከመሰላችሁ ለእዚህ አንድ ጥያቄ ብቻ መልስ ይስጡ፡፡ አንዲት ቤተ ክርስቲያን አንዴከተደራጀች በኃላ እንደቀድሞ ዓይነት የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ወይም መነቃቃት እንደነበራት የሚኖር ሰው ሊኖር ይችላልን? ታሪክዎን ያንብቡ። አንድም እንኳ ማግኘት አይችሉም፡

እስራኤል ከዓለም ጋር ስትቀላቀል እና ለፖለቲካ ብላ መንፈሳዊዉን ነገር ስትተዉ እኩለ ሌሊት ነበር፡፡ ቤተክርስቲያኑ ተመሳሳይ ነገር ያደረገችበት በኒቂያ እኩለ ሌሊት ነበር፡፡ አብያተ ክርስቲያናት አንድ ላይ እየተሰበሰቡ ያሉት አሁን እኩለ ሌሊት ነው፡፡

አሁን አክዓብ ኤልዛቤል ባገባት ጊዜ የስቴቱን ገንዘብ እንድትወስድና ሁለት ታላላቅ የአስታሮትና የበአል አምልኮ ቤቶችን እንድትሠራ ፈቀደላት፡፡ ለበኣል የተገነባው መላው እስራኤል እንዲመጣና አምልኮ እንዲያደርግ የሚያስችልግዙፍ ነበር፡፡ ቆስጠንጢኖስ እና ቤተክርስቲያን ሲጋቡ ለቤተክርስቲያኒቱህንፃዎች ሰጠ፣ መሠዊያዎችን እና ምስሎችን አቆመ እና ቀድሞውኑ እየተቀረጸ የነበረውን የሥርዓት አደረጃጀት አደራጅቷል፡፡

ኤልዛቤል የመንግስቱን ስልጣን ከእሷ በስተጀርባ ስላገኘች ሃይማኖቷን በሕዝቡ ላይ በግድ በማስገደድ የእግዚአብሔርን ነብያቶች እና ካህናትን ገደለች፡፡ ሁኔታው በጣም መጥፎ ከመሆኑ የተነሳ የዘመኑ መልእክተኛው ኤልያስ ብቻውን የቀረ ሰው መስሎት ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለበአል ያልሰገዱ7000 ተጨማሪ ነበሩት። እናም አሁን በእነዚያ የባፕቲስት፣ ሜቶዲስት ፣ የፕሬስባይቴሪያኖች ወዘተ የሀይማኖት ድርጅቶች መካከል በመዉጣት ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱ ጥቂቶች አሉ፡፡ አሁን እኔ ከህዙቡ ጋር ተቃዉሞ እንደሌለኝ እንድታዉቁ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ የምቃወመው የድርጅት ስርዓቱን ነው፡፡ እኔ እሱን መቃወም አለብኝ ምክንያቱም እግዚአብሔር ይጠላዋልና፡፡

አሁን እዚህ አንድ ደቂቃ እንቁም እና በትያጥሮን ውስጥ ስላለው አምልኮ ያወጣውን እንመልስ፡፡ አፖሎን(የፀሐይ አምላክ የተባለዉን) ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ያመልኩ ነበር ብዬ ተናግሪያለዉ፡፡ አሁን ይህ አጵሎስ 'የክፉ ጠላቂ' ተብሎ ተጠርቷል። ከሰዎች ክፉን የሚያርቅ፡፡ ባረካቸው ለእነርሱ እውነተኛ አምላክም ነበር፡፡ ስለ አምልኮ፣ እና ስለ መቅደስ አምልኮ፣ ለአማልክት ስለ አገልግሎት፣ ስለ መስዋእትነት እና ስለ ሞት እና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት እሱ ሰዎችን ማስተማር ነበረበት፡፡ ይህን ያደረገበት መንገድ በ ‹ሶፊያ› ወንበር ላይ በተቀመጠ ግርማዊት በነቢይ በኩል ነበር፡፡ ዎዉ! ይሄን ታያላችሁ? ኤልዛቤል የተባለችው ነብይ ሴት እዚህ አለች እና ሕዝቡን እያስተማረች ነው። ትምህርቷም የእግዚአብሔር አገልጋዮችን እያሳትና ዝሙት እንዲፈፅሙ እያደረገ ነው፡፡ ዝሙት ማለት ‹ጣዖት አምልኮ› ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ትርጉሙ ያ ነው። ህገ-ወጥ ህብረት ነው፡፡ የአክዓብ አንድነት እና የቆስጠንጢኖስ ህብረት ሁለቱም ሕገ ወጥ ነበሩ፡፡ ሁለቱም መንፈሳዊ ምንዝር ፈፀሙ፡፡ ሴሰኛ ሁሉ በእሳት የእሳት ሐይቅ ውስጥ ይጣላል። እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና፡፡

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን።

የውርድ(እንግሊዝኛ)... Jezebel Religion.


  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤

የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።

የዮሐንስ ራእይ 2:26-28


የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።
በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይቀጥላል።
(ምስጢር ባቢሎን።)



መልዕክት ሃብ...ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።


የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

ሰባት ማኅተሞች
ተከታታይ።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet.

(PDF እንግሊዝኛ)

The Two Babylons

by Rev Alexander Hislop.
(PDF እንግሊዝኛ)

ቻይና ውስጥ በረዶ ውስጥ
አንዲት ተራራ እና
የጽጌረዳን።

የእሳት በአበቦች።

የእሳት ዓምድ
- የሂዩስተን 1950።

አንድ ፒራሚድ ዓለት
ላይ ብርሃን ነው።

እናም በዚህ
የቲያጢሮን
ቤተክርስቲያን ዘመን
እርሷ የበላይ የሆነች
ሴት ናት፡፡ እሷ
ሚስጥራዊ ባቢሎን ነች።