የቤተ ክርስቲያንዘመን መግቢያ።


  የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።

እስያ የተቀመጡት።


William Branham.

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን።

የቤተ ክርስቲያንዘመን መልእክትን ሙሉ በሙሉ እንድትረዱት የመልእክተኞቹን ስም፤ የዘመናቱን ርዝመት ሌሎች ተካተው ያሉ ጉዳዮችን ማወቅ እንድችልየረዱኝን ልዩ ልዩ ቀኖናዎች ወይም መመሪያዎች ለማብራራት እወዳለሁ።

ይሄ ጥናትተከታታይ ከሆኑ ትምህርቶች መሐል ዋነኛው እንደመሆኑ እስከዚች ሰዓት ድረስ አልጀመርኩትም ነበር። ብዙ ቀናቶች እግዚአብሔርበመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ምሪትን ሲሰጠኝ አይቻለሁ። ከዛም ስለቤተ ክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን አነበብኩ የብዙ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አዋቂዎችያለ አድሎአዊነት ተጽፈው ያገኛኋቸውን አጥብቄ ፈለኩ እግዚአብሔርም ጸሎቴን ዝም አላለም ለብዙ ጊዜያት መጽሐፍ ቅዱስን እናታሪክን አንብቤያለሁ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነትም አሁን እስካለንበት የመጨረሻ ዘመን ድረስ በየዘመናቱ የነበረውን ንድፍ ማወቅችያለሁ።

የእያንዳንዱዘመን መልእክተኛ ማን እንደሆነ ለመለየት ከጌታ የተሰጠኝ ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ነው። በእውነታውም ከሆነ የመጽሐፍቅዱስ የመሠረት ድንጋይ ነው። የማይለዋወጥ ከእግዚአብሔር ያገኘሁት መገለጥነው የእርሱም አካሔዶች እንደማይለዋወጡ ሁሉ ዕብራዊያን13፡8 እንዲህ ይላል

“ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።”

መጽሐፈመክብብ 3፡14-15
“እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፤ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፤እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።
አሁን ያለው በፊት ነበረ፥ የሚሆነውም በፊት ሆኖ ነበር፤ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል።”

ይሄው እዚህጋር፡ የማይለዋወጠው አምላክ በማይለዋወጠው መንገዱ መጀመሪያ ላይ ያደረገው ነገር እስከ መጨረሻው ድረስ እስኪከናወን መቀጠልአለበት። መቀያየር የሚባል ነገር የለም። ይሄንን ለእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ዘመን ተግባራዊ አድርጉት። እግዚአብሔርለመጀመሪያው ዘመን የመረጠው የሰው አይነት እና በዛ ሰው የአገልግሎት ሕይወት ውስጥ የተገለጡት ነገሮች ለተቀሩት ለሁሉምዘመናት ተምሳሌት ይሆናል። እግዚአብሔር በመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ዘመን ያደረገው ነገር በተመሳሳይ መልኩ ነው ለተቀሩትዘመናትም ማድረግ የሚፈልገው።

አሁንበመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቃሉ ላይ የሰፈረውን የመጀመሪያይቱ ወይም የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደተመሠረተች እናእግዚአብሔር እንደተገለጠባት በትክክል ማወቅ ችለናል። ቃሉ አይቀየርም ወይም ሊቀያየር አይችልም ምክንያቱም ቃሉ እግዚአብሔር ነውና።ዮሐንስ1፡1

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”

በራእይ22፡18-19 ላይም እንደሚናገረው ልክ ሔዋን እንዳደረገችው በቃሉ ላይ መጨመር ወይም መቀነስ ኃጢአትን እና ሞትን ያስከትላል።

“ስለዚህበባለ ሐምሳው ቀን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን መለኪያችን ነች። ያ ነው ንድፉ ሌላ ንድፍ የለምምሁራኖች ኃጢአት ምንም ይበሉምንም ያንን ንድፍ እግዚአብሔር አልቀየረውም። እግዚአብሔር በባለሐምሳ ቀን ያደረገውን በየአብያተ ክርስቲያናት ዘመናቱ ሁሉማድረጉን ይቀጥላል።”

ምናልባትምሁራኖች የሐዋርያት ዘመን አብቅቷል ብለው ቢነግሯችሁ መቼም አትመኑአቸው። በሁለት ምክንያቶች ይህ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል።የመጀመሪያው አስራ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ስለሞቱ ብቻ ሌሎች ሐዋርያት የሉም ብሎ ማሰብ ስህተት ነው ሐዋርያ ማለትየተላከ ማለት ነው እናም ዛሬ ላይ ብዙ የተላኩ አሉ ነገር ግን ሚስዮን ተብለው ይጠራሉ አንድ ሰው ከተጠራ እና ሕይወት ባለውቃል ከተላከ የሐዋርያት ዘመን ቀጥሏል ማለት ነው። ሁለተኛ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፍ ከተጠናቀቀ በኃላ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልየተገለጠበት ዘመን አብቅቷል በማለት ይጠቅሳሉ ያ ደግሞ እውነት አይደለም። ይህን ጥቅስ የሚደግፍ አንዳች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልየለም በሐዋርያት ስራ 2፡38-39 ላይ ለሁለቱም ምክንያቶች ማረጋገጫው ተቀምጣል

“ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውናአላቸው።”

በባለ ሐምሳውእለት ለሐዋርያቱ የተሰጣቸው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ ቃል ለእናንተ(አይሁድ) ለልጆቻችሁ (አይሁድ) እና በሩቅ(አህዛቦች)ላሉ ነውና ጌታ እግዚአብሔር የቱንም ያህል ቁጥር ያላቸውን (ሁለቱም አይሁድ እና አህዛብ) ለጠራቸው ሁሉ ነው። እርሱ መጥራጡንእስካላቆመ ድረስ የባለሐምሳው ቀን መልእክት እና ኃይል ሊቆምአይችልም።

በባለ ምሳቀን ቤተ ክርስቲያን የነበራት ሁሉ የማይቀያየር መብት ነው። በዋናነት ንጹህ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነበራት በልዩ ልዩምልክቶች እና ድንቆች የተገለጠ የእግዚአብሔር መንፈስ ኃይል እና የመንፈስ ቅዱስስጦታ ነበራት። ዕብራዊያን 2፡1-4 ስለዚህከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።

“በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስእንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ አጸኑት፥ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንምበማደል አብሮ መሰከረለት።”

የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በሰው አልነበረም የተመሠረተችው። የምትመራው በመንፈስ ቅዱስ ነበርብዛትም አልነበራቸውም። ይጠሉ እና ይናቁም ነበር። ይጨቆኑ ነበር። እስከሞት ድረስ ይሰደዱ ነበር። ለእግዚአብሔር ግን እውነተኞችነበሩ። ከዋናው የቃል ንድፍ ጋር ቆይተው ነበር።

አሁ ንአግዚአብሔር እና መንገዶቹ አይቀያየሩም ስላልኩ በተሳሳተ መንገድ እንዳትመሩ ቤተ ክርስቲያን እና መልእክተኞች አይቀየሩምአላልኩም። ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር አይደለችም። ስለዚ እርሷ ልትቀየር ትችላለች ነገር ግን ያልኩት ነገር መንድን ነውበማይቀያየረው አምላክ እና መንገዶቹ ምክንያት ወደ ጅማሬው ወደ ኋላ ተመልሰን የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ እና ፍጹም የሆነውንአሰራሩን በመመልከት ያንን መለኪያ አድርገን መፍረድ እንችላለን። አደራረጉ እንደዛ ነው። እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜየመጀመርያይቱን የባለሐምሳ ቀን አይነት ቤተ ክርስቲያንን ለመምሰል ትጥራለች። ዛሬ ላይ ያለችውም ቤተ ክርስቲያን ያቺንየመጀመሪያይቱን ቤተ ክርስቲያን ለመምሰል ትጥራለች። እንዲሁም የየአብያተ ክርስቲያኑ መልእክተኞች በውስጣቸው አንዱንየእግዚአብሔር መንፈስ ይዘው ሐዋርያው ጳውሎስን ለመምሰል ይጥራሉ። ሙሉ በሙሉ እርሱን ላይመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛመልእክተኛ ከየትኛውም ሰው ነጻ የሆነ፤ ለእግዚአብሔር የተሸጠ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ የሚሰጥ፤ የመንፈስ ቅዱስም ኃይልይገለጥበት ከነበረው ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በደንብ የሚቀርብ መሆን አለበት። ካልሆነ ግን አይሆንም። ከዋናው።

ከመጀመሪያውመስራት አለባችሁ ልክ የወለደ የወለደውን እንደሚመስለው እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም በባለሐምሳ ቀን የወለዷትን የመሠረቷትንየእግር ዱካ የምትከተል ናት። እናም መልእክተኞቿም የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ የሆነውን ሐዋርያው ጳውሎስንይከተላሉ። ያን ያህል ቀላል እና ድንቅነው።

በዚህ ቀላልበሚመስል እናግሩም በሆነ ቁልፍ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የራእይን መጽሐፍ በማንበብ እና ታሪክን በማንበብ የእያንዳንዱን ዘመን፤እያንዳንዱን መልእክተኛ፤ የዘመን እርዝማኔውን እና በየዘመኑ ሁሉም በእግዚአብሔር ኃይል ከባለሐምሳ ቀን አንስቶ አሁንእስካለንበት የዘመን ፍጻሜ ድረስ የተጫወቱትን ሚና መለየት ችያለሁ።

አሁን እውነተኛይቱቤተ ክርስቲያንን እንዴት መፍረድ እንደምንችል ስለተረዳችሁ ልክ(በባለሐምሳ ቀን ትመስል የነበረውን እና በሐዋርያቱ ዘመንትመስል የነበረውን በሐዋርያት ስር መጽሐፍ ላይ በቃሉ እንደተቀመጠው) ያንን ተመሳሳይ መርህ በመጠቀምም እንዴት ቤተ ክርስቲያንእንደወደቀች ማየት እንችላለን። መሠረታዊ ስህተቶችን ወደ መጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ሾልከው የገቡትን በሐዋርያት ስራ መጽሐፍእና በራእይ መጽሐፍ እንደተገለጠው እንዲሁም ሐዋርያቱ በጻፏቸው ደብዳቤዎችም ወይም መልእክቶች በበለጠ እና በበለጠ መልኩበተከታታይ ዘመናት ላይ ሲገለጥ እናያለን እስከ መጨረሻዋ ሎዶቂያ ዘመን ድረስ እውነት እንዴት ሙሉ በሙሉ እንደጠፋ እንመለከታለን።

አሁን ከጌታካገኘነው የመጀመሪያው ቁልፍ ሌሌ ግሩም የሆነ እውነታ ይወጣል ቀደም ሲል እንዳልኩት እውነተኛ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜምበሐዋርያት ስራ ላይ የነበረውን ለመምሰል ትጥራለች ያ ደግሞ ትክክል ነው። ጌታ ሊገለጥ ባለበት ዘመን ደግሞ እውነት እስክትጠፋድረስ የስህተት ወረራ እንደሚሆን ከቃሉ አስተምህሮት ማወቅ ችለናል። አሁን በአይምሮአችን ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ እግዚአብሔርየራሱ የሆኑትን እረስቶ ሙሉ በሙሉ እንዲታለሉ ያደርጋል ወይ? በምንም ዓይነት ሒሳብ አይተዋቸውም በማቴ 24፡24 ላይ በግልጽመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና የተመረጡት ሊታለሉ አይችሉም።

“ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”

ስለዚህከዛስ? መልሱ በፊታችን ግልጽነው እውነተኛ እና ሐሰተኛ ቤተ ክርስቲያን አሉ እውነተኛ እና ሐሰተኛ ግንድ አሉ ነገር ግንበርግጥ ያቺ ሐሰተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ሐሰተኛዋ ግንድ የእውነተኛዋን ቤተ ክርስቲያን ቦታ ለመያዝ እና የተመረጠችው ሳትሆንእርሷ ብቻ ትክክል እና እውነተኛነቷ የተረጋገጠ እንደሆነች ለማስመሰል ትሞክራለች። ሐሰተኛዋ እውነተኛዋን ለመግደል ትሞክራለችበሐዋርያት መጽሐፍ ላይ የነበረው ይሄ ነው። በሰባቱም ዘመናት የሆነውም ይሄ ነው በተለያዩ የሐዋርያቱ ደብዳቤ የተገለጸው በዚሁመልኩ ነው። በፊትም እንደዛ ነበር አሁንም እንደዛ ነው ወደ ፊትም እንዲሁ ይቀጥላል። አይቀየርም።

----
እነዚህ ሰባቱአብያተ ክርስቲያናት በታናሿ እስያ የተቀመጡት በውስጣቸው የየራሳቸው ልዩ ባህርያትን ይዘዋል ያኔ የነበረው ዘመን የመጪው ዘመንየበሰለ ፍሬ የሆነ ነው ያኔ እዛ ተዘርቶየነበረው ዘር አድጎ በሚታጨድበት ዘመን ይወጣል ልክ ኢየሱስ እንደተናገረው። ሉቃስ23፡31
“በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ እንዴት ይሆን?”

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን።



የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።
በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይቀጥላል።
(ዕድሜያችን ፣ ሎዶቅሳ።)


የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

ሰባት ማኅተሞች
ተከታታይ።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።

አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

ትንቢተ ዘካርያስ 14:6-7


ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet

(PDFs እንግሊዝኛ)

God, Hidden and
Revealed in simplicity.

(PDF እንግሊዝኛ)

William Branham
Life Story.

(PDF እንግሊዝኛ)

How the Angel came
to me.

(PDF እንግሊዝኛ)


 


መልዕክት ሃብ... ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።