የውኃ ጥምቀት።


  የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ።


William Branham.

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ።

የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ እንደሆነ ለማየት መገለጥ ያስፈልጋል ይህን እዉነት እንዳይመለከቱ ሰይጣን ሰዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶአታሏል፡፡ በዚህ መልኩም ሲታለሉ ያን ያህል እሩቅ አልነበረም የሮማ ቤተ ክርስቲያን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቅ ካቆመች በኋላ ነዉ፡፡

ብዙ ሊያደናብሩ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ባለንበት በእነዚህ ቀናቶች ስለ ሙላተ መለኮት ጉዳይ በርግጥ እዉነተኛ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ እንደሚያስፈልግ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን የቤተ ክርስቲያን የመቋቋሚያ እና ማሸነፊያዋ የተመሠረተዉ በመገለጥ ላይ ብቻ ነዉ ስለሆነም ለሁላችንም እዉነቱን ይገልጥልን ዘንድ እግዚአብሔርን እንጠብቀዋለን፡፡ ሐዋርያቱ ከጌታ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከሆነዉ በአብ፤ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም የማጥመቅ ትእዛዝ ትክክለኛ መንገድ ወጥቶ ለመሄድ ለደቂቃ እንኳን የሚችሉ ይመስላችኋል በፈቃዳቸዉ የማይታዘዙ? እነርሱ ስሙ ማን እንደሆነ ያዉቃሉ ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዉጪ ያጠመቁበት አንዳች ቦታ አታገኙም፡፡

የሐዋርያት ስራ መጽሐፍ የቤተ ክርስቲያን ተግባር እንደሆነ የተፈጥሮ እዉቀት እንኳን ይነግራችኋል እናም እነርሱ በዛ መልክ ካጠመቁ ስለዚህ የማጥመቂያ መንገዱ እሱ ነዉ ማለት ነዉ ይሄ ጠንከር ያለ ነዉ ብላችሁ ካሰባችሁ ማንኛዉም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያልተጠመቀ ሁሉ ዳግም መጠመቅ አለበት ስለሚለዉ ጉዳይስ ምን ታስባላችሁ?

የሐዋርያት ስራ 19፡1-6,
“አጵሎስም በቆሮንጦስ ሳለ ጳዉሎስ በላይኛዉ አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን አላቸዉ እነርሱም አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት እንኪያበምን ተጠመቃችሁ አላቸዉ እነርሱም በዮሐንስ ጥምቀት አሉት ጳዉሎስም ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንሰሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸዉ ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ ጳዉሎስም እጁን በጫነባቸዉ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸዉ በልሳኖችም ተናገሩ፡፡ ሰዎችም ሁሉ አሥራ ሁለት ያህሉ ነበር፡፡”

ይሄዉ እዚጋ እነዚህ በኤፌሶን ያሉ መልካም ሰዎች ስለሚመጣዉ መሲህ ሰምተዉ ነበር በንስሐ ጥምቀትም ወደፊት የሚመጣዉን ኢየሱስን ተመልክተዉ ተጠምቀዉ ነበር አሁን ግን ወደኃላ ወደ ኢየሱስ ተመልክተዉ ለኃጢአት ስርየት መጠመቅ አለባቸዉ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የመቀበያ ጊዜ ነዉ ልክ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስስም ሲጠመቁ ጳዉሎስ እጁን ጫነባቸዉ እናም መንፈስ ቅዱስ በላያቸዉ ላይ ወረደ፡፡

ዉድ ወዳጆቼ ሆይ በኤፌሶን እንዳሉት ሰዎች መልካም ሰዎች ደህንነታቸዉ የተጠበቀ እንደሆነ እንደተሰማቸዉ የሚሰማችሁ ሰዎች ካላችሁ ምን ያህል እርቀት ተጉዘዉ እንደመጡ አስተዉሉየሚመጣዉን መሲህ እሰከመቀበል ደርሰዉ ነበር እርሱን ለማግኘት ዝግጁ ነበሩ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች እሱን አለማግኘታቸዉ ብቻሳይሆን መጥቶ ዳግም ተመልሶ ሄዷል በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ ያስፈልጋቸዉ ነበር በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ያስፈልጋቸዉነበር፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከተጠመቃችሁ እግዚአብሔር በመንፈሱ ይሞላችኋል ይህ ቃሉ ነዉ፡፡

ቀደም ሲል ያነበብነዉ ሐዋ ስራ 19፡6 የሐዋ ስራ 2፡38ቃል ፍጻሜ ነዉ,
“ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡”

ተመልከቱ ጳዉሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የተናገረዉን እራሱን ተናገረየተነገረዉ ቃል ደግሞ አይቀየርም፡፡ ከባለሃምሳ ቀን አንስቶ የመጨረሻዉ የተመረጡ ሁሉ እስኪጠመቁ ድረስ ተመሳሳይ መሆን አለበት ገላቲያ 1፡8,
“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፡፡”

አሁን አንዳንድ ኢየሱስ ብቻ የምትሉ ሰዎች አጠማመቃችሁ ስህተት ነዉ፡፡ የምታጠምቁት በጠለቀ ዉኃ ዉስጥ መጠመቅ ብቻ እንደሚያድን አድርጋችሁ ሰዎችን ለመዳን ነዉ የምታጠምቁት መዳን በዉኃ ጥምቀት አይገኝም የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነዉ፡፡ በመንፈስ ተመርቶ ትእዛዙን ያስተላለፈዉ ሰዉ እንዲህ ብሎ ነዉ “ንስሐ ግቡ እናም በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ” እዚህ ላይ ውኃው ያድናል አላለም ያለዉ ተግባሩ “ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነዉ፡፡” ይሄዉ ነዉ፡፡

1ኛ ጴጥሮስ 3፡21,
“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል የሰዉነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነዉ እንጂ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ነዉ፡፡”
እኔ አምነዋለሁ፡፡

ታሪክ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዉጪ ጥምቀት እንዳለ ያረጋግጣል የሚል የተሳሳተ ሐሳብ ያለዉ ሰዉ ካለ እራሳችሁ ታሪኩን አንብባችሁ እንድታረጋግጡ ምክር እሰጣለሁ፡፡ ቀጣዩ ታሪክ በሮም አገር ኢየሱስ ከሞተ ከ 100 አመታት በኃላ ታየም ተብሎ በሚታወቅ መጽሄት ላይ የተመዘገበ እዉነተኛ የሆነ የጥምቀት ድርጊት ነዉ እ.አ.አ ዴሴምበር 5 1955 ዓ.ም

“ዲያቆኑ እጁን ወደ ላይ አነሳ እና ፐብሊዩስ ዲሲዩስ ወደ ማጥመቂያ በር ዘለቀ በማጥመቂያ ገንዳ ዉስጥ እስከ ወገቡ ድረስ ጠልቆ የቆመዉ እንጨት ሻጩ ማርከስ ቫስካ ነበር ፐብሊዩስ በማጥመቂያ ገንዳ ዉስጥ ከአጠገቡ መጥቶ ሲቆም ፈገግ እያለነበር፡፡ ክሪድስ ብሎ ጠየቀ ክሪዶም ለፐብሊዩስ እንዲህ ብሎ መለሰለት በጲላጦስ ግዛት ስር ለመስቀል ሞት ታልፎ በተሰጠዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መዳኔ እንደሚገኝ አምናለሁ የዘላለም ህይወት አገኝ ዘንድ ከእርሱ ጋር አብሬ ሞቻለሁ ካለ በኃላ ወደኃላ እራሱን ወደ ዉሃ ሊያስገባ ሲል ጠንካራ ክንድ ሲደግፈዉ ተሰማዉ ከዛም ወደ ቀዝቃዛ ዉሃ ዉስጥ እየሸፈነዉ በጌታ ኢየሱስ ስም አጥምቅሃለሁ” የሚል የማርከስ ድምጽ ተሰማ፡፡

እዉነታዉ እስከጠፋበት ጊዜ ድረስ(እዉነቱ እስከተመለሰበት አሁን እስካለንበት ዘመን ማለትም ከኒቂያ ጉባኤ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ) ጥምቀት ይከናወን የነበረዉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነበር፡፡ አሁን ግን ተመልሶ መጥቷል መንፈስ መገለጥን ሊሰጥ ሲፈልግ ሰይጣን መገለጡን ሊያስቆም አይችልም፡፡

አዎ ሦስት አምላክ ቢኖር ኖሮ በአባት፤ በልጅ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማጥመቁ መልካም ይሆን ነበር ነገር ግን ለዮሐንስ የተሰጠዉ መገለጥ አንድ አምላክ እንዳለ ብቻ ነዉ ስሙም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ እምናጠምቀዉም አንድ እና አንድ በሆነዉ አምላክ ብቻ ነዉ፡፡ ለዛም ነዉ ጴጥሮስ በባለሐምሳ ቀን ባጠመቀበት መልኩ ያጠመቀዉ ለተሰጠዉ መገለጥ እዉነተኛ እና ታማኝ መሆን ነበረበት “በርግጥ የእስራኤል ወገን ሁሉ እግዚአብሔር እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገዉ ይህን ይወቅ፡፡” ይሄዉ እዚህ ጋር “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ”

ኢየሱስ ሁለቱንም ጌታ እና ክርስቶስ ከሆነ ስለዚህ እርሱ(ኢየሱስ) እራሱ አባት፤ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ነዉ እንጂ ሌላ ሊኖር አይችልም በአንድ አካል በስጋ ተገለጠ እንጂ በሦስት አካል ዉስጥ ያለ አንድ አምላክ አይደለም የሥላሴ አማኞችን እግዚአብሔር ይባርካቸዉ ነገር ግን አንድአምላክ አንድ አካል በሶስት ታላላቅ መገለጫዎች እና ስያሜዎች የተገለጠ ነዉ፡፡ ጌታ(አብ) እና ክርስቶስ(መንፈስ ቅዱስ)ኢየሱስ ነዉ ምክንያቱም እርሱ (ኢየሱስ) ሁለቱንም ስለሆነ (ጌታም ክርስቶስም)

ይሄ የሙላተ መለኮትን እዉነተኛ መገለጥ ሊያሳየን ካልቻለ ሌላ ሊያሳየን የሚችል ነገር የለም፡፡ ጌታ ማለት ሌላ አይደለም ክርስቶስ ማለት ሌላ ማለት አይደለም ይሄ ኢየሱስ እራሱ ነዉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ - አንድ አምላክ፡፡ ፊሊጶስ አንድ ቀን ለኢየሱስ እንዲህ አለዉ “ጌታ ሆይ አብን አሳየን እናይበቃናል ኢየሱስ መልሶ ይሄን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስሆን አታዉቀኝምን እኔን ያየ አብን አየ ስለምን አብን አሳየን ትላለህ እኔ እና አብ አንድ ነን፡፡”

----
እግዚአብሔርን በሦስት አካል ወይም በሦስት ክፍል ልናስቀምጥ አንችልም፡፡ ለአንድ አይሁዳዊ አባት ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ብለህ ልትነግረዉ አትችልም ይሄ ሀሳብ ከየት እንደመጣ በፍጥነት ይነግርሃል አይሁዶች ይሄ እምነት የተመሠረተዉ በኒቂያ ጉባዔ ላይ እንደሆነ ያዉቁታል፡፡ ልክ እንደ አረመኔ አድርገዉ ቢንቁንም አያስደንቅም፡፡

ስለማይቀየረዉ አምላክ አወራን ይሄን አይሁዶችም ያምኑታል፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የማይለወጠዉን አምላክ ከአንድ ወደ ሦስት ለወጠችዉ ሆኖም ግን በጨላማዉ ሰዓት ብርሃኑ ተመልሷል እንዴት ያለ የሚደንቅ ነገር ነዉ ይሄ እዉነት እስራኤላዊያን ወደ ፓልስቲን በተመለሱበት ወቅት መምጣቱ እግዚአብሔር እና ክርስቶስ አንድ ነዉ ይሄ ኢየሱስ ጌታም ክርስቶስም ነዉ፡፡ ዮሐንስ መገለጥ ነበረዉ መገለጡም ኢየሱስ ነበር እራሱንም በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ገለጸዉ - “እኔ ያለ፤ የነበረ፤ የሚመጣ እኔ ነኝ ሁሉን ቻይ አሜን”

መገለጡ ከእናንተ በላይ ከሆነባችሁ ወደ ላይ ቀና ብላችሁ እግዚአብሔርን ተመልከቱት ማግኘት የምትችሉበት ብቸኛ መንገድ ይሄ ነዉ፡፡ መገለጥ ከእግዚአብሔር ብቻ ይመጣል በሰዉ በኩል፤ በተፈጥሮ በኩል ሳይሆን በመንፈሳዊ መገኘት ብቻ ይመጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አሥሬ ብታሰላስሉት ያ መልካም ቢሆንም እንኳን ያም ግን አይሰራም ከእግዚአብሔር ብቻ የሚመጣ መገለጥ መሆን አለበት በቃሉ ላይ እንዲህ ይላል በመንፈስ ካልሆነ በቀር ሰዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ ሊል አይችልም መንፈስ ቅዱስና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነዉ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀባዉ አምላክ ነዉ እንድትሉ መገለጥን የሚሰጣችሁ፡፡

የእግዚአብሔር መንፈስ ሊገልጥለት ካልወደደ ወይም ሊያድነዉ ካልወደደ በቀር የእግዚአብሔርን ነገር ሊያዉቅ የሚችል ሰዉ የለም፡፡ በአለም ላይ ካለዉ ከምንም ነገር በላይ መገለጥን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ልንጠራዉ ያስፈልጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ተቀብለናል በዉስጡ ያለዉንም ታላቅ እዉነት ተቀብለናል ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ባለመኖሩ የተነሳ ለብዙ ሰዎች እዉነት አይመስላቸዉም ቃሉ አላነቃቃቸዉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በ2ኛ ቆሮንጦስ 5፡21 ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት የእግዚአብሔር ጽድቆች እንደሆንን ይናገራል፡፡ አገኛችሁት በክርስቶስ በመሆናችን በራሱ በእግዚአብሔር ጸድቀናል ይላል እርሱ(ኢየሱስ) ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ፡፡ ኃጢአተኛ ሆነ አይልም፡፡ ከእርሱ ጋር በሚኖረን ኅብረት የእግዚአብሔር ጻድቃን እንሆን ዘንድ ለእኛ ኃጢአት ሆነ ነዉ የሚለዉ፡፡

እዉነታዉን እንቀበል ካልን (የግድም መቀበል አለብን)በእኛ ምትክ ፋንታ ቀጥታ ኃጢአት እንደሆነ ስለዚህ ከእርሱ ጋር ባለን ኅብረት ደግሞ የእግዚአብሔር ጻድቃን የመሆናችንን እዉነታ መቀበል ይገባናል፡፡ አንዱን አለመቀበል ሌላኛዉን አለመቀበል ነዉ አንደኛዉን መቀበልም ሌላኛዉን መቀበል ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ እንደሚል እናዉቃለን፡፡ ሊካድ የሚችል አይደለም፡፡ ስለዚ ጉዳይ ያለዉ መገለጥ ግን ተዘንግቷል ለብዙኃኑ የእግዚአብሔር ልጆችም በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለ አንድ ጥሩ ጥቅስ ሆኖ ይታሰባል እንጂ የምር እዉነታ እንደሆነ አይታሰብም በሕይወታችን ሕያዉ እንዲሆን ማድረግ አለብን፡፡ ይህም ደግሞ መገለጥ ያስፈልገዋል፡፡

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ።



የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።
በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይቀጥላል።
(ምስጢር ባቢሎን።)




 

የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።

ሰባት ማኅተሞች ተከታታይ።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት። ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው።

ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

የሐዋርያት ሥራ 2:36-39


ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet.

(ፒዲኤፍች እንግሊዝኛ)

ጋብቻ እና ፍቺ።

(ፒዲኤፍ)

ከዚህ በፊት።...

በኋላ ነው።...

የኔ የህይወት ታሪክ
ዊልያም ብራናም።

(ፒዲኤፍ)

How the Angel came
to me.

(ፒዲኤፍ እንግሊዝኛ)


መልዕክት ሃብ...ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።