ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ቃል።

<< ቀዳሚ

ቀጣዩ >>

  ኑሮ ቃል ተከታታይ።

ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ቃል።

ከ...  ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ምሥጢር ነው።


William Branham.

ከምንም በላይ ደግሞ እርስ በእርስ ተዋደዱ። እርስ በእርስ ተዋደዱ።ዲያብሎስ የፈለገውን ለማለት ይሞክር... እናንተ አንድ ታላቅ ውብ እና ድንቅ ቡድን ናችሁ፡ እናም ማስጠንቀቂያየን አስቡ!አያችሁ? ሰይጣን እንዲህ ሆኖ እንድትቀጥሉ አይፈልግም። በፍጹም ወዳጄ! አንድ አንድ የማያምን ነቃፊ አምጥቶ፡ ከእናንተ ጋር በእርጋታእያመለከ እንዲቀመጥ ያደርገዋል፥ ከዛ በኋላ በመርዛማ ነገር ይመርዘውና፡ ቸርቿን ሊረብሽ ይጀምራል። እንዳትተባበሩት! ከእንደዚሁ ዓይነት ጋር ምንም ነገር አይኑራችሁ! እርስበእርሳችሁ ቅኖች፣ መልካሞች፣ ሩህሩሆች እየሆናችሁ ተዋደዱ። ለዛ ወንድ ወይም ለዛች ሴት የትኛውም ይሁን እንዲድኑ ጸልዩላቸው።በቃ ጸልዩላቸው፡ እርስ በእርስም በአንድነት ተያያዙ፡ ከፓተራችሁም ጋራ አንድ ሆናችሁ ቆዩ። አያችሁ? እሱ እረኛ ነው፡ እናንተምአክብሩት። ይሄን ለማድረግ በጌታ የተቀባ ነውና፡ በነገር ሁሉ ይመራችኋል።

እንግዲህ፡ ጠላት ይመጣል። አትረሱም አይደል? ሲመጣም አብልጣችሁበአንድነት ተያያዙ። ከዛ በኋላ ያ ጠላት ለክፋት ሲጠቀምበት የነበረውን ሰው፡ ወይ ገብቶ ከእናንተ እንደ አንዱ ይሆናል ወይም ደግሞይሄድላችኋል። በመካከላችሁ ምንም አነት ጎሳዊ ንግግር አትናገሩ፡ ራሳችሁን አንድ ጎሳ አድርጉ፡ አንድ ነን። “ግራ እጄን፡ በጣም ተበሳጭቼብሀለሁ፡ ቀኝ እጅ ስላልሆንክ ገንጥየ እጥልሀለሁ” ልል አልችልም። ግራ እጄ ነው። እዛው በቦታው እንዲሆንልኝ እፈልገዋለሁ፣ ትንሿም ጣቴ እንዲሁም መላ አካላቶቼ በስፍራቸውእንዲቆዩልኝ እፈልጋቸዋለሁ። ጌታም እንደ የአማኞች አካል እርስ በእርስእየተደጋገፍን በስፍራችን አብረን እንድንሆን ይፈልገናል።

በዚህ ዙርያ ላይ ቴፖች አሉአችሁ። የምናምነውም በተመለከተ፣ በቤተክርስትያንባለ ስርዓት በተመለከተ፣ በጌታ ቤተክርስትያን ውስጥ ራሳችንን እንዴት መግዛት እንደሚገባን፣ አብረን በህብረት መጥተን እንዴት በሰማያዊስፍራ መገኘት እንደሚገባን የሚገልጹ ቴፖች አሉአችሁ። እቤት አትቅሩ። ጌታ በልባችሁ ከሆነ፡ በሮች ተከፍተውላችሁ ከወንድሞቻችሁጋር ለማምለክ በጣም ትቸኩላላችሁ። እንዲህ የማይሰማችሁ ከሆነ ግን፡ መጸለይ እንዳለባችሁ እነግራችኋለሁ። ምክንያቱ መጽሓፍ ቅዱስ“ይልቁንስ ቀኖቹ ተቃርበው ስናያቸው፥ በክርስትያናዊ መሎኮታዊ ፍቅር እርስ ለእርስ አጥብቀን መዋደድ እንደሚገባን እና በክርስቶስኢየሱስ በሰማያዊስፍራ በሕብረት መሰባሰብ እንደሚገባን” ይመክረናል። “ሰዎች የኔን ደቀ መዝሙር መሆናችሁን እርስ በእርስ ስትዋደዱበፍቅራችሁ ያውቁአቹኋል።” ይህ እውነት ነው። በአንድነት ሁኑ።

ወንድም ነው የምትሉት ወይእህት ናት የምትሏት ተሳስቶ ካያችሁት “ጌታ ሆይ፡ መራራ ስር እንዳይበቅልብኝ እና እንዳልጎዳው፡ የክርስቶስን መብት ከህይወት እንዳላጣእርዳኝ” በሉ። ምክንያቱ ያንን የምቀኝነት እና የቅናት እንዲሁም የጥላቻ መርዛማ አሲድ መንፈስ ቅዱስን ከውስጣችሁ ያስሸሻልና።ከዚሁም ከጉባኤው ያስሸሻል። የጌታን መንፈስ ይገድላል እንዲሁም ከዚህ እንዲርቅ ያደርገዋል፣ ፓስተራችሁንም ያስመታል፣ ሁሉም ነገርያደርጋል። ፈጽማችሁ እንዳታደርጉት! ይሄን ያህል በአንድነት ቅለጡ። ወንድማችን (ያ አገልጋይ) ባለፈው ማታ ላይ ዘለበቱን በተመለከተ (በራእይ አይቶ ) እንደሰጠን ምስክርነት፡ ዘለበቱን አንሱ። ዘለበቱንም በጌታ ጦር ዕቃ ላይ ውሰዱ፥ አጥብቃችሁም ታጠቁት፥ እርስበእርስ ተጠጋግታችሁ ተያያዙ። በምንም ዓይነት ሁኔታ ይሁን እርስ በእርስ ተዋደዱ። እርስ በእርስ መልካምን ተነጋገሩ፡ ከዛ በኋላምጌታ ይባርካችኋል።

ከ...  ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ምሥጢር ነው።


  ኑሮ ቃል ተከታታይ።

የእግዚአብሔር የመራባት ህግ።

ከ...  የጴርጋሞንም ቤተ ክርስቲያን ዘመን፡፡


William Branham.

“ለእናንተ ልነግራችሁ የፈለኩት ነገር ይሄን ነዉ የመባዛት ህግ እያንዳንዱ ዝርያ የራሱን አምሳይ የራሱን ወገንመምሰል አለበት በዘፍጥረት 1:11,ላይ እንኳን ” እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬንየሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።“ ይላል፡፡ በዘሩ ዉስጥ ያለዉ ህይወት ምንም ይሁን ምንምወደ እጸዋትንት እና ወደ ፍሪነት ይመጣል ተመሳሳይ የሆነዉ ህግም ዛሬ ላይ ላለችዋ ቤተክርስቲያንም ይሰራል፡፡ ቤተክርስቲያንየጀመረችዉ የትኛዉም አይነት ዘር መዉጣትእና የመጀመሪያዉን ዘር መምሰል አለባት ምክንያቱም ተመሳሳይ ዘር ነዉና በዚህየመጨረሻዉ ዘመንም እዉነተኛ ሙሽሪት ቤተክርስቲያን (የክርስቶስ ዘር) ወደ ማእዘኑ እራስ ትመጣለች እናም ታላቅ ቤተክርስቲያንትሆናለች ታላቅ ዘር ወደ እርሱ በተጠጋች ቁጥር በሙሽራይቱ መካከልም እርሱን ይመስሉታል ይሄም ከእርሱ ጋር ህብረት ለማድረግነዉ አንድ ይሆናሉ፡፡ ህያዉ የሆነዉ የእግዚአብሔር ቃል መገለጫዎች ይሆናሉ የሐይማኖት ድርጅቶች ይሄን ማፍራት አይችሉም(የስህተት ዘሮች) የራሳቸዉን ቀኖና እና ህግ ያመጣሉ ከቃሉ ጋር ይቀላቅሉታል ይሄም መደባለቅ የተቀላቀለ ዉጤት ያመጣል፡፡

የመጀመሪያዉ ልጅ (አዳም) የተነገረየእግዚአብሔር ቃል ዘር ነዉ ራሱን እንዲያባዛም ሙሽሪት ተሰጠችዉ ለዛ ነዉ ሙሽራይቱ የተሰጠችዉ ራሱን እንዲያባዛ ሌላየእግዚአብሔር ልጅ እንዲያመጣ ነገር ግን እሷ ወደቀች በመቀላቀሏ ምክንይት ወደቀች እንዲሞት ምክንያት ሆነች፡፡

ሁለተኛዉልጅ (ኢየሱስ) የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ዘር ሙሽሪት ተስጥቶታል ልክ እንደ አዳም ነገር ግን እሷን ከማግባቱ በፊት እሷምወደቀች እሷ ልክ እንደ አዳም ሚስት የእግዚአብሔርን ቃል አምና ትኖራለች ወይስ ቃሉን ተጠራጥራ ትሞታለች የሚለዉን ነገርለማወቅ ፈተና ዉስጥ ገባች፡፡

እዉነተኛ ዘር ከሆኑት ትንሽ ቡድኖች መካከልእግዚአብሔር ክርስቶስን በተወደደችዋ ሙሽሪት ራሱን ያቀርባል እሷ የቃሉ ድንግል ነች ድንግል ነች ምክንያቱም ማንም ሰዉ የራሱንቀኖና እና ህግ ማዉጣት እንደማይችል ታዉቃለች፡፡ የሙሽራይቱ አባል በመሆን እግዚአብሔር በድንግል ይፈጸም ዘንድ የሰጠዉ ተስፋቃል ሁሉ ይፈጸማል፡፡

ለድንግል ማርያም የተሰጠዉ ተስፋ ቃልተሰጠ፡፡ ነገር ግን የተሰጠዉ የተስፋ ቃል እራሱ ነበር እንዲገለጥ እግዚአብሔር ተገለጠ እርሱ እራሱ በድንግሊቱ ዉስጥ የሰጠዉንተስፋ ቃል ፈጸመዉ መልእክቱን ያመጣላት መላእክ ነበር ነገር ግን የመላእኩ መልእከት የእግዚአብሔር ቃል ነበር ኢሳያስ9፡6 የተነገረዉንቃል ሁሉ በዛ ጊዜ ስለእርሱ ተጽፎ የነበረዉን ፈጸመዉ ምክንያቱም ቃሉን ለራሷ ተቀብላ ስለነበር፡፡ የድንግሊቱሙሽራይት አባል የሆነችዉ እርሱን ትወደዋለች እርሱም የእነርሱ እራስ ስለሆነ በእርሱ ዉስጥ ያሉት አቅሞች እና ሀይሎች ሁሉይኖራቸዋል የአካላችን ክፍሎች ሁሉ ለእራሳችን እንደሚገዛ እሷም ለእርሱ ትገዛለች፡፡

የአባትና የልጅን ቅንጅት አስተዉሉት ኢየሱስ አባቱ ካላሳየዉ በቀር አንዳች ነገርን አያደርግም ነበር ዮሐንስ5፡19ይሄ አንድነት አሁን በሙሽራዉ እና በሙሽሪት መካከል የሚሆን ነዉ እርሱ የህይወትን ቃል አሳይቷታል ተቀብላዋለች አትጠራጠረዉምስለዚህ ምንም ሊጎዳት አይችልም ሞትም እንኳ ቢሆን አንድ ዘር ከተዘራ በኃላ ዉሃ ዳግም ያነሳዋልና የዚህ ሚስጥር ይሄ ነዉ ቃሉበሙሽሪት ዉስጥ ነዉ (በማሪያም ዉስጥ እንደነበረዉ) ሙሽራይቱ የክርስቶስ ልብ አላት በቃሉ ምን ማድረግ እንዳለባት ታዉቃለችናበቃሉ ዉስጥ ያለዉን ትእዛዛት ሁሉ በስሙ ታከናዉናለች “ጌታ እንንዲህ ይላል” የሚለዉ ቃል ስላላት ከዛም ቃል በመንፈሱአማካኝነት ያልፋል ልክ እንደተተከለና ዉሃ እንደሚጠጣ ዘር አላማዉን ለማገልገልሙሉ በሙሉ እንደሚሰበሰበዉ ይሰበሰባል፡፡

በሙሽራይቱ ዉስጥ ያሉ ሁሉ ፈቃዱን ይፈጽማሉ ማንም እንዲህ አድርጉ አይላቸዉም “ጌታ እንዲህ ይላል” የሚለዉ ቃልአላቸዉና፡፡ ወይም ይጠብቃሉ፡፡ በእነሱ ዉስጥ ሆኖ የእራሱን ቃል እየፈጸመ ስራዉን የሚሰራዉ እግዚአብሔር እንደሆነ ያዉቃሉበምድር ላይ የነበረዉን አገልግሎቱን አላጠናቀቀም ስለዚህ በሙሽራይቱ ዉስጥ እና በኩል ይፈጽመዋል፡፡ ይሄን ታዉቃለች አንዳንድአሁን ማድረገ ያለበትን ነገሮች ያኔ ጊዜዉ እንዳልነበረ ታዉቃለች፡፡

አሁንልክ እንደ ኢያሱ እና ካሌብ እንነሳ የተስፋይቱ ምድር ያኔ እንደታየቻቸዉ በፊታችን ትታያለች ኢያሱ ማለት “ያህዌ አዳኝ” ማለትሲሆን በመጨረሻዉ ዘመን ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣዉን መሪ ያሳያል ልክ ጳዉሎስ የመጀመሪያዉ መሪ እንደነበረ፡፡ ካሌብ ደግሞ ከኢያሱጋር በእዉነት አብረዉ የቆዩትን ያመላክታል፡፡ አስታዉሱ እግዚአብሔር እስራኤልን የቃሉ ድንግል አድርጎ ነዉ ያስጀመራት ነገር ግንሌላ የተለየ ነገር ፈለጉ የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ይታያል እግዚአብሔር እስራኤልን ወደ ገባላትየተስፋይቱ ምድር እራሱ በቀጠረዉ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ እንድንትንቀሳቀስ ወይም እንድትገባ እንዳላደረጋትም አስተዉሉት አሁን ምናልባህዝቡ በኢያሱ ላይ “ምድሪቱ የእኛ ናት ሔደን እንያዛት ሊሉት ይችላሉ በዚህ ሁሉ ኢያሱ ስራህን እረስተሐል ያኔ የነበረህ ሐይልአሁን የለም ከእግዚአብሔር ትሰማ እና ምሪትን ታዉቅ ነበር የሆነ ችግር አለብህ፡፡” በማለት ሕዝቡ ግፊት ሊያድርበት ይችላል ነገርግን ኢያሱ ከእግዚአብሔር የተላከ ነብይ እና የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል የሚያዉቅ ነዉ ስለሆነም እነሱን ጠበቃቸዉ ከእግዚአብሔርቁርጥ ዉሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ዝም አለ እናም የሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሲመጣ እግዚአብሔር ሙሉ አመራሩን በኢያሱ እጅ አኖረ ምክንያቱምከቃሉ ጋር ተጣብቆ ቆይታልና፡፡ እግዚአብሔር ሌሎቹን ሳይሆን ኢያሱን ብቻ ያምነዉ ነበር፡፡ ስለዚህ ይሄዉ ተመሳሳይ ችግር በዚህበመጨረሻዉ ዘመንም ይደገማል ተመሳሳይ ችግር፤ተመሳሳይ ግፊት፡፡

ከ...  የጴርጋሞንም ቤተ ክርስቲያን ዘመን፡፡


የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

ሰባት ማኅተሞች
ተከታታይ።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።

እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤

ትንቢተ ኢሳይያስ 60:1-2


ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet

(PDF እንግሊዝኛ)
 

ክርስቶስ የተገለጠው
የእግዚአብሔር ምሥጢር
ነው።
(PDF)

ከዚህ በፊት።...

በኋላ ነው።...

William Branham
Life Story.

(PDF እንግሊዝኛ)

How the Angel came
to me.
(PDF እንግሊዝኛ)


መልዕክት ሃብ...ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።