የእግዚአብሔር ዓላማ።
<< ቀዳሚ
ቀጣዩ >>
ክርስቶስ የተገለጠው የአምላክ ሚስጢር ነው።
William Branham.ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
ክርስቶስ የተገለጠው የአምላክ ሚስጢር ነው።አስተውሉ፡ ጌታ ሶስት መዐዝናዊየሆነ ታላቅ እንቆቅልሻዊ ሚስጢር ነበረው። የጌታ እንቆቅልሻዊው ሚስጢር ዓለም ከመጀመሩ በፊት የነበረ ሚስጢር ነው። በውስጡም ሶስትመአዝናዊ ዓላማ አለው። እንግዲህ አሁን በዚሁ ማለዳ ልናየው የምንፈልገውም፥ ይህ ሶስት መአዝናዊ የጌታ ዓላማ ምንድነው ነው? አያችሁ?እንግዲህ በጌታ እርዳታ እና በመገኘቱ - እንደሚያሳየን አምናለሁ። እንግዲህ ሶስት መአዝናዊዓላማ ከነበረው... እነዚያ ሶስት መአዝናዊ ዓላማዎች ምን እና ምንድን ነበሩ ብለን መፈተሽ እንፈልጋለን።
የመጀመርያው ነገር፥ አምላክ ራሱን ለህዝቦች ማስተዋወቅ ወይም መግለጽ እንደሚፈልግ ነው። ይሄን ለማድረግ ሰማየ ሰማያትን እንዲሁም ጊዜ እና ዘለአለማዊነትንየሚሞላ ጆሆቫ ሆኖ ይህን ማድረግ አይቻለውም። ለሰዎች ከተገለጠ ነገር ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነው፥ ምክንያቱ በጣም እንቆቅልሻዊ ስለሆነ።ይህ መጀመርያ የሌለው... ወደ መቶ ቢልዮኖች እና ትሪልዮን ትሪሊዮኖች ብርሀን ዓመታት ስትመለሱ፥ ማለቅያ ወደሌለው ዘለአለማዊነት፣ታላቁ ፈጣሪ ይህ ሁሉ የነበረ ነው፣ አሁንም ያለው እሱ ነው።
ማድረግ የፈለገው ታድያ ምንድነው? እሱ አባት ስለነበረ አባትነትን ወደደ። አባትነቱን የሚገልጽበትብቸኛው መንገድ ደግሞ የሰው ልጅ በመሆን ነበረ። ለዛም ነው ኢየሱስ በተደጋጋሚ “የሰው ልጅ” ሲል የነበረው። አያችሁ አብዛኞቻቸው፡የሚናገራቸው ነገሮች አይረዱትም ነበር። አሁን ግን፥ ገብቶአቿል? ራሱን ማሳየት መግለጽ ወደደ። ያ ደግሞ ከሶስት ማአዝናዊ ሐሳቦቹአንዱ ዋናው ሐሳቡ ነበር። ራሱን በክርስቶስ ለመግለጽ ራሱን ከሰው ልጆች ጋር አንድ ማድረግ ነበረበት።
ሁለተኛም፡በህዝቡ በሰዎች መካከል ይኖር ዘንድ፥ በእሱ አማኖች አካል ማለትም በሙሽራይቱ ላይ እንዲሰለጥን።
ይሄንን ነገር አስቀድሞ በአዳም እና በሄዋን ውስጥ ማድረግ ይችል ነበር ቢሆንም ግን ሐጢአት ለያያቸው፡ስለዚ ያንን የሚመልስ መንገድ ያስፈልግ ነበር። ኦ ማይ! ኦ ይሄንን ሳስብ በጣም ያረካኛል! የጌታ አላማ ምን እንደነበር አያችሁ? አዳምን እና ሄዋንን እንዲሁለምን አይተዋቸውም ነበር? እንዲያማ ከሆነ ሙላቱን፣ ሙሉ መገለጫዎቹን በትክክል መግለጽ በፍጹም አይቻለውም ነበር። ምክንያቱ እዛምሆኖ አባት መሆን ይቻለው ነበር፥ ነገር ግን ደግሞ አዳኝም ነው። “አዳኝ እንደነበረ እንዴት አወቅህ?” ብትሉኝ፥ ልምምዱ ስለነበረኝእሱ አዳኝ ነው። አያችሁ! እሱ አዳኝ ነው። አዳኝነቱንም ማስተዋወቅ ነበረበት። ታድያ እንዴት ነው ማስተዋወቅ የሚችልበት? በክርስቶስበኩል ብቻ ነው። እንዴት ብሎ ነው ልጅ መሆን የሚችለው? - በክርስቶስበኩል ነው። እንዴት ብሎ ነው ፈዋሽ የሚሆነው? በክርስቶስ በኩል ብቻ ነው። አያችሁ፡ ይህ ሁሉ በአንድ ሰው - ኢየሱስ ክርስቶስይጠቃለላል። ኦ ማይ!
ይኄንን ሳስብ፥ የሀይማኖትተቋማቶቹ ከመስመር ሲወጡ ሌላውም ሁሉ እንዲሁ ሲሆን ይታየኛል። ጌታ ራሱን የማስተዋወቅ ወይም የመግለጽ ታላቁን ዓላማ ስመለከት- መጀመርያ ራሱን የአንድ አምላክ መለኮት ሙላት በስጋ በክርስቶስ ውስጥ ሲገልጽ፥ ከዛም በኋላ የተገለጸውን የመሎኮት ሙላት፡ በሰዎችላይ የበላይ፣ አለቃ እና መሪ ሊያደርገው በስጋ ወደ ሰዎች አመጣው።
እንዲሁም ባለፈው... አንድ ቀን ማታ፥ ጳውሎስ እስረኛው... የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ በሚል እዚህ የሰበክኩት የስብከት ካሴት ካላገኛችሁ... አምላክ እስረኞችሁ ሊያደርጋችሁ ከያዛችሁ፥ መንፈሱ ከሚለው ውጪ ለማለት ዕድል አታገኙም። ጳውሎስ፡ ከታላቅ እውቀቱጋራ - አንድ ቀን ታላቅ ካህን ወይም ራቢ እንዲሆን ታላቅ ምኞት የነበረው በገማልኤል የተማረ ሰው ነበረ። በእውቀት የላቀ ሰው- በአገሪቱ የከበረ ታላቅ ባለስልጣን ነበረ። ይሁን እንጂ፡ የቃሉን አካል እንዲሆን፥ ክርስቶስ ኢየሱስን በሌሎች ፊት መግለጽ እንዲችል፡ይህ ሁሉ መስዋዕት ማድረግ ነበረበት። ምን ማለት እንዳለበት የሚያውቅ ነው... (ውንድሞች ጠርተውት) ወደ አንድ ስፍራ ለመሄድሀሳብ ነበረው፥ ይሁን እንጂ የገዛ ፈቃዱን እንዳያደርግ በመንፈስተከለከለ። ኦ! እነዚያ ግማሽ መንፈሳዊያን ሰዎች ይሄንመረዳት ቢችሉ! ገዛ ፈቃዱን እንዳያደርግ ተከለከለ። ብቸኛው ማድረግ የሚችለውነገር... “መንፈስ ከልክሎኛል።” አያችሁ? የክርስቶስ እስረኛነበረ።
ያቺ ኮኮብ ቆጣሪ ሴት'ኮ- ጳውሎስ ዲያብሎሱን ከሷ ገስጾ ማውጣት የሚችልበት ሀይል እንደነበረው ያውቅ ነበር፡ ይሁን እንጂ ያንን ማድረግ የሚችለው አምላክሲፈቅድለት ብቻ ነበር። እናም ከኋላው እየጮሀች በየእለቱ ተከተለችው፥ አንድ ቀን ግን መንፈስ ፈቀደለት። ከዛም በኋላ በውስጣ የነበረውንመንፈስ ገሰጸ። አያችሁ! እስረኛ መሆን ምን እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ሙሴን ብንመለከት፡ እሱክርስቶስን እንዲያገኝ፡ የሱ እስረኛ እንዲሆን የነበረው እውቀት ሁሉመጣል ነበረበት። ጌታ በውስጡ የነበረውን ታላቅነት እና ዓለማዊነት ከውስጡ ቀጥቅጦ፥ በእሳት ዓምድ የተገለጠለት ዕለት ቃላት አጥሮትዝም አለ። መናገር የማልችል ተብታባ ነኝ ሳይቀር አለ። ስለዚ አምላክ እስረኛ አገኘ። በራሳችሁ መንገድ እንዳትሞክሩት። ከዛ በኋላአምላክ ይሄንን ሰው ማስታጠቅ ነበረበት - ወደዛ መውረድ የሚችልበትን በቂ ሀይል አስታጠቀው። እንዲም አለ “ጌታ ሆይ፡ ያልከኝንፈርኦንን ነገርኩት እሱ ግን እምቢ አለ።” አለ።
“ይሄን በትርህን ውሰድ (የጌታ ቃል ነው)፡ እዛ ሂድ እና ብትርህን ወደ ምስራቅ በኩልዘርጋው ዝንቦችም ጥራ” አለው። ዝንቦችም ተፈጠሩ፡ ምክንያቱ ፈርኦን ሊያስቆመው ያማይችል እስረኛ ስላገኘ። ማንም ሰው በምንም መልኩ ሊመልሰው አይቻለውም። በአምላክ ቃል ሰንሰለት የታሰረ እስረኛ፣ ለጌታ ሰራዊት እንዲህ ይላል ፈጽሞ የታሰረ እስረኛ።
አምላክ እስረኖቹን እንደዛ ማግኘት ከቻለ! ያኔ ነው በላያቸው ላይ ልዕልናውን መግለጽ የሚችለው።ከክርስቶስውጪ ምንም ሌላ ነገር እንዳያውቅ ሰውየውን ይይዘዋል። ምን ለማለት እንደፈለግኩ ገባችሁ? መልካም። ይሄንን ሁለተኛው ነው። አንደኛው፥ አምላክ ራሱንሙሉ በሙሉ በክርስቶስ መግለጽ። ሁለተኛው በዚህም (በአካሉ ማለትም በሙሽራይቱ) ላይ የበላይነትን፣ ልዕልናን እንዲያገኝ። ራሱንበእነሱ ለመግለጽ ያንን ልዕልና መያዝ አለበት። መልካም እንግዲህ።
ሶስተኛውም በመጀመርያውሰው አዳም በሐጢአት ምክንያት ወድቆ የነበረውን መንግስት ወደ ትክክለኛው ስፍራ ከህዝቡ ጋር በየማታው ወደሚሄድበት፣ የሚነጋገርበት፣ ሕብረትየሚያደርግበት ምቹ ስፍራ፣ ማቃናት። ሓጢአት እና ሞት ከህልውናው እና ከአጠቃላይ መገለጫዎቹ ለያይቶአቸው ነበር። ገብቶአቿል?... ከዓለም ምስረታ በፊት ማንነቱን እና መገለጫዎቹን ሁሉ ለማስተዋወቅ።
ስለዚ፥ ስላሴአውያን እዚህ ካላችሁ፡ ለአንድ ደቂቃ ራሳችሁን ፈታ አድርጉ እና ይህን ተመልከቱ፡ አባት ልጅ እና መንፈስቅዱስ የአንዱ አምላክ ሶስት መገለጫዎችእንጂ ሶስት አማልክቶች አይደለም። አባት መሆን ፈለገ። አባትነት - መገለጫ (መዐርግ) ነው። አባት ነበረ፣ ልጅ ነበረ፣ አሁንምመንፈስቅዱስ ነው። አይታያችሁም ወይ? ገባችሁ? - ሶስት አማልክት አይደለም። ዲያብሎስ ጣኦትን በመካከላችሁ ለማድረግ የነገራችሁነገር ነው። በሶስት መገለጫዎች የተገለጠ አንድ አምላክ ነው። አባት ለመሆን፣ አዳኝ ለመሆን፣ ልጅ ለመሆን፣ ፈዋሽ ለመሆን (አያችሁ?)- መገለጫው ነው።
በቴፕ ካሴት የሚሰሙ ሰዎች ሃሳቡን በደንብ እንዲረዱት፡ ማየት እንዲችሉ የተወሰነውን እነካካዋለሁ። ርእሶቹ ሁሉ የየራሳቸው ሰዐት ሊወስዱብኝ ይችሉ ነበር።ይሁን እንጂ፡ ወደምን እየመጣሁ እንደሆነ በተወሰነ መልኩ ማየት እንደቻላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
ጌታ የአንድ አምላክን ሙላት፥አባትም ልጅም መንፈስቅዱስም በነበረው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በአካል ተረከው። አሁን የአንዱ አምላክ ፍጹም የመለኮት ሙላት- ገዢነት በቤተ ክርስትያን ውስጥ ሰፍሯል። አምላክነት የሆነውን ሁሉ ወደ ክርስቶስ ጨመረው፥ ክርስቶስ ውስጥ የነበረውን ሁሉ ደግሞወደ ቤተክርስትያን - ማለት ወደ ሀይማኖት ተቋም ሳይሆን ወደ አማኞችጨመረው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ወደዛ እንገባለን፡ ከአእምሮአችሁም ውስጥ ለዘለአለም ይወስደዋል። አያችሁ። ከፈቀዳችሁልኝ፥ በጌታእርዳታ ያንን የሆነበት ምክንያት ምን እንደሆነ አሳያቹኋለሁ።
እንግዲህ ዓላማው ታድያ ምንድነው? - ዓላማው የአንድ አምላክ የመለኮት ሙላት ሁሉ በእሱ በስጋው እንዲያድር ራሱን እንደ ልጅ መግለጽ (ማስተዋወቅ) ነው።ቆላይስይስ በፊቴ ተዘርግቶ አየዋለሁ... በቃላቱ ሁሉ የጌታዓላማው ይህ ነበር።
በዚህ የልጅ ህይወት፥ በመስቀሉ(በመስቀሉ ደም) አንድ አካል ሙሽራ (ሄዋን - ሁለተኛዋ ሄዋን) ከራሱ ጋር የሚያስታርቅ ከሆነ፤ በአዳም እና በሄዋን ያደረገውንያንኑ ጥላ፥ በሙሽራይቱ እና በክርስቶስ መካከል መሆኑን ለማሳየት አምላክ በሙሴ እና በሌሎች ሁሉ ጥላ ሲሰጥ ነበረ (እሱ ሁለተኛውአዳም ነው፣ ቤተክርስትያኒቱም ሁለተኛዋ ሄዋን ናት) ሁለተኛዋ ሄዋን... “ይሄንን እማ ለሌላ ዘመን ነበር” እያለች በቃሉእስካመቻመቸች ድረስስ፡ የመጀመርያዋ ሄዋን ያደረገችው ተመሳሳይ ድርጊት እያደረገች አይደለችም ወይ? እሱ ለሌላ ዘመን ብሎ እንደሆነና እንዳልሆነ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንደርስበታለን። እሱ ትላንትናናዛሬ እስከ ለዘለአለም ያው ሆኖ ሳለ! እንዴት ነው ለሌላ ዘመን ሊሆን የሚችለው! ነገር ግን ጌታ፡ ከጥበበኞች እና ከአስተዋዮችዓይን ሰውሮ፥ አስቀድሞ ለወሰናቸው - ሕጻናት - አስቀድመው የተወሰኑ እንዲቀበሉት አድርጎ ወስኖት ነበር።
ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
ክርስቶስ የተገለጠው የአምላክ ሚስጢር ነው።
ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።
Acts of the Prophet. (PDF እንግሊዝኛ) |
ጋብቻ እና ፍቺ። (PDF) |
William Branham Life Story. (PDF እንግሊዝኛ) |
How the Angel came to me. (PDF እንግሊዝኛ) |