የራዕይ መጽሐፍ፡፡
የዮሃንስ ራእይ።
William Branham.ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ።የዮሐንስ ራእይ 1:1-3,
“ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባዉን ነገርለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠዉ በእርሱም የተገለጠዉ ይህ ነዉ፡ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባርያዉለዩሐንስ አመለከተ እርሱም ለእግዚአብሔር ቃል እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየዉም ሁሉ መሰከረ፡፡ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበዉየትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በዉስጡ የተጻፈዉን የሚጠብቁት ብጹዓን ናቸዉ፡፡”የዚህ መጽሃፍ ጸሀፊ ወይም ደራሲ ቅዱስ ዮሃንስ ሳይሆን ደራሲዉ አምላክነዉ የታሪክ አጥኒዎች እንደሚስማሙት ዮሃንስ የመጨረሻዉን ህይወቱን የኖረዉ በኤፌሶን ሲሆን ይሄን መጽሃፍ የጻፈዉም ጲጢሞስ በምትባልደሴት ዉስጥ ነዉ፡፡ ነገር ግን ቁጥር 3 ላይ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙት ብሎ እንደሚገልጸዉ ወደፊት በሚመጡት የአብያተክርስቲያናትዘመን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ያሳያል በትክክልም የሆነዉ ይህ ነዉ፡፡
ይህ መጽሃፍ በተለምዶ የዮሃንስ ራእይ ተብሎ ቢሰየምም ስህተት ነዉ ትክክለኛዉመሆን ያለበት በሁሉም የአብያተ ክርስቲያናት ዘመን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነዉ፡፡ ለዮሃንስ የታየ ወይም የተሰጠ መገለጥ ነዉ፡፡
በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ የመጨረሻዉ መጽሃፍ ነዉ ነገር ግን የወንጌልን ጅማሬእና መደምደሚያ የሚነግረን መጽሃፍ ነዉ፡፡
በግሪክ መገለጥ የሚለዉ ቃል አፖካሊፕስ ሲሆን ይህም ማለት ገለጠ ማለትነዉ፡፡ ይህ መገለጥ አንድ የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያተኛ የሀዉልት ስራዎቹን ለተመልካቾቹ እንደሚገልጥበት ምሳሌ በደንብ ተገልጿል በፊትተከድኖ የነበረዉን መግለጥ ማለት ነዉ፡፡ የተከፈተዉም የኢየሱስ ክርስቶስ በአካል መገለጥ ብቻ ሳይሆን በሚመጡት ሰባቱ አብያተክርስቲያናትምዘመን የሚገለጥበትን መገለጥ ጭምር ነዉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ መገለጥ ለእዉነተኛ አማኝ የሚሰጠዉ ጥቅም ፈጽሞ የማይጋነን ነዉ እናንተ ከምታስቡት በላይ መገለጥ እጅግ አስፈላጊ ነዉ፡፡እያወራሁ ያለሁት መገለጥ ለሁሉም አይነት መገለጥ ነዉ ለቤተክርስቲያን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡ ታስታዉሳላችሁ በማቴዎስ 16 ላይ ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶቹን እንዲህብሎ ሲጠይቃቸዉ “ሰዎች የሰዉን ልጅ ማን ይሉታል” እነርሱም እንዲህ አሉት አንዳንዶችመጥምቁ ዩሃንስ ነዉ ይላሉ፤ አንዳንዶች ኤልያስ ይላሉ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነብያት አንዱ ነዉ ይላሉ፡፡ እርሱም መልሶእንዲህ አላቸዉ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ እናም ስምኦን ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰ አንተ የተቀባህ የህያዉ የእግዚአብሔር ልጅ ነህኢየሱስም መልሶ የዮና ልጅ ስምኦን ሆይ የተባረክህ ነህ እነሆ ስጋ እና ደም ይህን አልገለጠልህም በሰማይ ያለዉ አባቴ ገልጦልሃልና እነሆ እላችኋለሁ ጴጥሮስ ሆይ በዚህ አለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እገነባለሁየገሀነም ደጆችም ሊቋቋማት አይችሉም፡፡ የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችዉ በጴጥሮስ ላይ ነዉ ይላሉ ይሄ ከስጋነዉ ምክንያቱም በምን አይነት መንገድ ነዉ እግዚአብሔር ባልተረጋጋ እና ኢየሱስን በካደዉ ሠዉ ላይ ቤተክርስቲያኑን የሚገነባዉ እግዚአብሔርከሐጥያት በተወለደ በማንም ሰዉ ላይ ቤተክርስቲያኑን ሊገነባ አይችልም፡፡ የሆነ ቦታ ላይም እግዚአብሔር ቀድሶ ባቀመጠዉ አለት ላይምአይደለም የተገነባችዉ በመገለጥ ላይ ነዉ፡፡ እስኪ እንደተጻፈዉ መንገድ አንብቡት “ስጋና ደም አልገለጠልህም ነገርግን በሰማይ ያለዉ አባቴ ገለጠልህ እንጂ እናም በዚህ አለት (መገለጥ) ላይ ቤተክርስቲያኔን እገነባለሁ ፡፡ቤተክርስቲያን የተገነባችዉ በመገለጥ ላይ ነዉ “እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል”
አቤል ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘዉን መስዋእት ማቅረብ እንዴት አወቀ?በእምነት ለመስዋእትነት ደም ማቅረብ እንዳለበት መገለጥን ተቀበለ፡፡ ቃየን ግን ይሄን መገለጥ አላገኘም (ምንምታዛዥ ቢሆንም እንኳን) ስለሆነም ተገቢ የሆነዉን መስዋእት ማቅረብ አልቻለም፡፡ ልዩነትን ያመጣዉና አቤልን የዘላለም ህይወት የሰጠዉ ከእግዚአብሔር ያገኘዉመገለጥ ነዉ፡፡ የሚያነጻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሆነና የሚያድናችሁ እግዚአብሔር እንደሆነ እግዚአብሔር እስኪገልጥላችሁድረስ መጋቢዎች የሚነግሯችሁ ወይም በየሴሚናሩ የሚያስተምሩት የሚያኮራ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚያስገባችሁመንገድ መገለጥ ብቻ ነዉ፡፡
ቀደም ሲል እንዳልኳችሁ ይህ የራእይ መጽሀፍ የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥእና በሰባቱ የአብያተ ክርስቲያናት ዘመን የሚሰራቸዉን ተግባራት የሚገልጽ መጽሃፍ ነዉ፡፡ ይህ መገለጥ ነዉ ምክንያቱም ደቀመዛሙርቶቹእንኳን ይሄን የተጻፈዉን እዉነት አላወቁትም ነበርና ታስታዉሳላችሁ በሐዋርያት ስራ መጽሃፍ ላይ ወደ ኢየሱስ መጥተዉ ይሄን ጥያቄጠየቁት ''ጌታ ሆይ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግስትን ትመልሳለህን?'' እናም እንዲህ አላቸዉ “አብ በገዛ ስልጣኑ ያደረገዉንወራትና ዘመናት ታዉቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጠም” ደቀ መዛሙርቱ አሁንም ድረስ ኢየሱስ በምድር ላይ ያለ መንግስት እንደሚኖረዉእንደሚመሰረት ያስቡ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ሊገነባ ያለዉ መንፈሳዊ መንግስት ነበር በሚመሰርተዉ መንግስት የእርሱ ቦታ ምንእንደሆነ እንኳን አልነገራቸዉም አብ ለእርሱ አልገለጠለትም ነበርና ነገር ግን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኃላ በዚህ ጊዜ በማስታረቅአገልግሎቱ ላይ በቀጥታ ለዮሃንስ በመገለጥ ነበር የእሱን ክብር እና ከቤተክርስቲያን መገኘት ትርጉምና ተግባሩን ለመግለጥ የቻለዉ፡፡
በዚህ መገለጥ የሰይጣንን መጨረሻ ይነግረናል፡፡ ከዲያብሎስ ጋር እንዴትእንደሚጋፈጠዉ እና ወደ እሳት ባህር እንደሚጥለዉ ይነግረናል፡፡ ሰይጣንን የተከተሉ ሁሉ መጨረሻቸዉ ምን እንደሆነ ይገልጥልናል ይሄንመገለጥ ደግሞ ሰይጣን ይጠላዋል፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ መጻህፍቶች ዉስጥ ከሌሎቹ ይበልጥ ሁለት የሚጠላቸዉመጻህፍቶች እነማን እንደሆኑ ታስተዉላላችሁ? በስነ-መለኮት ሊቃዉንት እና በሀሰተኛ የሣይንስ ምሁራን በኩል የኦሪት ዘ ፍጥረት መጽሃፍንእና የራእይ መጻህፍን ሁለቱን መጻህፍት ሁልጊዜ ለማጥቃት ይሞክራል፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ መጻህፍት ዉስጥ የሴይጣንን መነሻ ክፉመንገዶች እና የመጥፊያ መንገዱን የምናገኝባቸዉ መጻህፍቶች ናቸዉ፡፡ ለዛ ነዉ ሁል ጊዜ የሚያጠቃቸዉ፡፡ መጋለጥን ይጠላዋልና፡፡በእነዚህ መጻህፍት ደግሞ ማንነቱ በትክክል የተገለጠ ነዉ፡፡ ኢየሱስ ስለ ሴይጣን እንዲህ አለ ከእኔ ጋር አንዳች ክፍል የለዉምእኔም አንዳች ህብረት የለኝም ዲያብሎስ ልዩነቱን ለማረጋገጥ ይፈልጋል ነገር ግን አልቻለም፡፡ ስለሆነም በቃሉ ላይ ሰዎች መተማመንእንዳይኖራቸዉ ለማድረግ የቻለዉን ሁሉ ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ሰይጣንን ማመን ሰትተዉ እና የቃሉን በመንፈስቅዱስመገለጥ ስታምን ያን ጊዜ የገሀነም ደጆች አይቋቋሟትም፡፡
ቅር የማይላችሁ ከሆነ እስኪ ከእራሴ የአገልግሎት ህይወት ልንገራችሁ በህይወቴ እየተገለጡ ያሉት ስጦታዎችከተፈጥሮ በላይ እንደሆኑ ሁላችሁም ታዉቃላችሁ በሰዎች ልብ የተሰወረን ሃሳብ እና የበሽታን አይነት መለየት እንዲሁም ሌሎችእግዚአብሔር ብቻ ሊያዉቃቸዉ የሚችሉነገሮችን ለእኔ የሚገለጥልኝ ከመንፈስቅዱስ የሚገኝ ስጦታ ብቻ ነዉ፡፡ ሰይጣን ሊጋለጥእንደሆነ ሲያዉቅ የሠዎች ፊት ላይ የሚነበበዉን ነገር ከአጠገቤ ቆማችሁ ብትመለከቱ ምኞቴ ነበር፡፡ አሁን እያወራሁ ያለሁት ስለሰዎች አይደለም የሰዎችን ህይወት በሃጥያት፤በግድየለሽነት እና በበሽታ የያዘዉ ሴጣን ነዉ፡፡ ነገር ግን ፊታቸዉን ስትመለከቱሴይጣን ሊጋለጥ እንደሆነ እንዳወቀ ታያላችሁ እናም እንግዳ የሆነ ለዉጥ በሰዎች ፊት ሲመጣ ታያላችሁ ይህም ሰይጣን ሲፈራነዉ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዎችን ነጻአዉጥቶ ሊያጋልጠዉ እንደሆነ ያዉቃል ለዛም ነዉ ይሔን መሰባሰባችንን አብዝቶየሚጠላዉ፡፡ ስሞች ሲጠሩ እና በሽታዎች ሲጋለጡ ሴይጣን ያን ይጠላዋል አሁን ይሄ ታዲያ ምንድን ነዉ ይህ የሰዎችን አእምሮማንበብ አይደለም ፤ በመንፈስ የሰዎችን አእምሮ ግንኙነትም አይደለም ወይም ጥንቆላም አይደለም ማወቅ የምችልበት መንገድ በመንፈስ ቅዱስ በኩል በሚገኝ መገለጥ ብቻ ነዉ፡፡ በርግጥ ስጋዊ የሆነ ሰዉ የፈለገዉን ነገር ብሎ ሊሰይመዉ ይችላልነገር ግን ይህ ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነዉ፡፡
በአብያተ ክርስቲያናት መካከል የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ የሚያሳየዉን ይሄን መጽሃፍሰይጣን የሚጠላበትን ሌላ ምክንያት ላሳያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትናም ዛሬም እስከለዘላለም የማይለዉጥ እና ያዉ መሆኑንየስነመለኮት አጥኚዎች ከሚያዉቁት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ ሙሉ በሙሉ ያዉቃል እግዚአብሔር የማይለዋወጥ አምላክ እንደሆነ ሁሉበሚሰራዉም የአሰራር መንገድ ተለዋዋጭ እንዳልሆነ ያዉቃል (ማርቆስ16 ላይ ያሉት ምልክቶች የሚከተላት ቤተክርስቲያን) ጌታኢየሱስ የእኔ ቤተ ክርስቲያን ብሎ የሚጠራት በእግዚአብሔር ሃይል የተመሰረተችዉ የመጀመሪያይቷ በባለሀምሳቀን የተጀመረችዉንእዉነተኛ ቤተክርስቲያን እንደሆነች ሌላዉ ሁሉ ግን ሐሰተኛ እንደሆነ በደንብ ያዉቃል፡፡
አሁን ይሄን አስታዉሱ ክርስቶስ በእዉነተኛይቷ ቤተክርስቲያን የሐዋርያት ስራ መጽሃፍቅጥያ ናት ነገር ግን የራዕይ መጽሀፍ የክርስቶስ ተቃዋሚዉመንፈስ እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ እንዳቆሸሻት፤በራድ ወይም ትኩስ እንዳትሆን እንዳደረጋት፤የተለመደ እና ሀይል የለሽእንዳደረጋት ያሳየናል፡፡ ሰይጣን እና ስራዉን ያጋልጣል (የእግዚአብሔርን ህዝብ ለማጥፋት እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማቃለልእንዴት እንደሚሞክር ያጋልጣል) ወደ እሳት ባህር እስከሚጣልበት ጊዜም እንደዚህ ለመዋጋት ይሞክራል፡፡ ነገር ግን መቆምአይችልም፡፡ እዉነተኛይቷ ቤተክርስቲያን ምን እንደሆነች፤ለምን አላማ እንደቆመች እንዲሁም ታላላቅ ስራዎችን የምትሰራ እንደሆነችሰዎች እዉነተኛ መገለጥ ማግኘት ከቻሉ ስዉር ሰራዊት እንደምትሆን ሰይጣን ያዉቃል፡፡ ክርስቲያን ተብሎ በሚጠራዉ ቤተክርስቲያን አዉድ ዉስጥ ስላሉት ሁለትአይነት መናፍስት እዉነተኛ መገለጥ ካገኙ እና በእግዚአብሔር የመለየት መንፈስ የክርስቶስ ተቃዋሚን መንፈስ መቋቋም ከቻሉሰይጣን በቤተክርስቲያን ፊት ሀይል አልባ ይሆናል፡፡
በርግጥም ክርስቶስ በምድረበዳ ዉስጥ ማሸነፍ እንደቻለ ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ መገታትይችላል አዎ ሰይጣን መገለጥን ይጠላል ነገር ግን እኛ ደግሞእንወደዋለን በህይወታችን በሚሆነዉ እዉነተኛ መገለጥ የገሀነም ደጆች ሊቋቋሙን አይችሉም ነገር ግን እኛ በላያቸዉ ላይእንቋቋመዋለን፡፡ አስቀድሜ መጀመሪያ አካባቢ ላይ ለመናገር እንደሞከርኩት ይህ እያጠናነዉ ያለነዉመጽሃፍ በቤተክርስቲያን ዉስጥ እና ወደ ፊት ባለት ዘመናት የሚሰራቸዉ ስራዎች እና የእራሱ የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን ነዉ መገለጡን ለማግኘት መንፈስ ቅዱስ የግድ ያስፈልገናልአለበለዚያ ግን መገለጡን ማግኘት አንችልም በማለት ለመግለጽ ሞክሪያለሁ ሁለት የተለያዩ ሃሳቦችን አምጥቶ የዚህ መጽሀፍ እዉነታላይ ለመድረስ አካል እንዲለብስ ለማድረግ የመንፈስቅዱስ ስራ ያስፈልገናል ያ ማለት ይሄ መጽሃፍ ለተለዩ ሰዎች ብቻ እንጂለማንኛዉም ሰዉ ሊገለጥ አይችልም፡፡ ትንቢታዉ እይታ ያለዉ ሰዉ መሆን ይጠይቃል ከእግዚአብሔርመስማትን ይጠይቃል ዝምብሎ እንደ አንድ ተማሪ ከአንድ ጥቅስ ወደ ሌላ ጥቅስ ማገላበጥ ብቻ አይደለም ምንም እንኳን ያ መልካምቢሆንም ነገር ግን ሚስጢር የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት ያስፈልገዋል ካልሆነ ግን መቼም ግልጽ ሊሆን አይችልም፡፡ እንዴትከእግዚአብሔር ማድመጥ እንደምንፈልግ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ክፍት ማድረግ እና ለመንፈስ መሸነፍ እና ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ቀደም ሲል እንዳልኩት ይህ መጽሀፍ (የራዕይመጽሃፍ) መጽሃፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ መረዳት ማለት ነዉ የተቀመጠዉም በመጨረሻዉየመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ነዉ፡፡ ስለዚ አሁን ለምን የትንቢቱን ቃል የሚያነበዉ ወይም የሚሰማዉ የተባረከ ነዉ እንዳለታዉቃላችሁ፡፡ በዲያብሎስ ላይ ስልጣንን የሚሰጣችሁ የእግዚአብሔር መገለጥ ነዉ እናም ከዚህ መጽሃፍ ላይ የሚጨምሩም ሆነየሚቀንሱ ለምን የተረገመ ይሁን እንደሚል ማየት ትችላላችሁ፡፡ በርግጥም እንዲህ መሆን አለበት ፍጹም ከሆነዉከእግዚአብሔር መገለጥ ተጨምሮ እና ተቀንሶ እንዴት ጠላትን ማሸነፍ ይቻላል ያን ያህል ቀላል ነዉ ከቃሉ መገለጥ ዉጪ መቋቋምየሚቻልበት አንዳችም ነገር አይኖርም ተመልከቱ ቁጥር 3 ላይ ለዚህ መጽሃፍ የተለየ ትኩረትለሚሰጡ በረከት እንዳለዉ ተገልጿል ይህ ደግሞ በብሉይኪዳን ዘመን የነበሩ ካህናት በማለዳ ለጉባኤዉ የሚያነቡትን ልማድሊያመላክት ይችላል አያችሁ ከካህናቱ በቀር ብዙዎች ማንበብ አይችሉም ስለሆነም ካህናቱ የግድ ያነቡላቸዉ ነበር ምንም ይሁንምንም የተነበበዉ ቃሉ እሰከሆነ ድረስ በረከት ነበረዉ፡፡
“ጊዜዉ አሁን ነዉ.” ከዚ ቀደም ጊዜዉ አልደረሰምነበር ይሄ ታላቅ መገለጥ በእግዚአብሔር ጥበብ እና እዉቀት (ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ የታወቀ ቢሆንም) እስከ አሁን ድረስ ግንአልመጣም ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ መመሪያን እንማራለን - ለእያንዳንዱ ዘመን የእግዚአብሔር መገለጥ ለዛ ዘመን ብቻ የሚገለጥመሆኑን፡፡ የእስራኤልን ታሪክ ተመልከቱ ለሙሴ የእግዚአብሔር መገለጥየመጣዉ በታሪክ ዉስጥ በአንድ በተወሰነ ጊዜ ብቻ እሱንም ህዝቡ ወደ እግዚአብሔር ባለቀሰ ሰአት ነበር ኢየሱስ እራሱ የሙላተመለኮት መገለጥ ሆኖ የመጣዉ ጊዜዉ በደረሰ ሰአት ነበር በዚህም ዘመን (በሎዶቂያ) የእግዚአብሔር መገለጥ በራሱ በተቀጠረለት ጊዜ ይመጣል ፈጥኖም አይደለም ያለጊዜዉም አይደለምይሄንን አስቡና አሁን ያለንበትን የመጨረሻ ዘመን ቆጥራችሁ ድረሱበት፡፡
ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ።