የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

የስህተት ዘር።


  የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

ዝናብ በጻድቁ እና በሐጥአን እንደሚዘንብ ሁሉ።


William Branham.

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ...
የስህተት ዘር።

ከሁለት ዓመታት በኋላ፤ ለጸሎት በምሄድበት በአንድ ኣቧራ የበዛበት ዋሻ በጸሎት ነበረኩ። አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ መጽሓፍ ቅዱሴን ግንድ ላይ አስቀምጬ ዞር ዞር እያልኩኝ ሳለሁ፤ ንፋስ ነፈሰና መጽሓፍ ቅዱሴን በዕብራውያን ምዕራፍ 6 ላይ ገለጠው፤ እንዲህ የሚለውንም ቃል አገኘሁ፥ “መልካሙን የእግዚኣብሄር ቃል ሊመጣ ያለዉን የዓለምን ሓይል የቀመስን በኋላም የካድን እንደገና ለንስሓ እኛን ማደስ የማይቻል ነው ለሓጢኣት የሚቀርብ ሌላ መስዋዕት የለምና። ለመጣል የቀረበ እሾህ እና ኩርንችት መጨረሻው መቃጠል ነው። ዝናብ ምድርን ሊያጠጣ እና ሊከድናት በተደጋጋሚ ይመጣላታል እሾህ እና ኩርንችቶቹ ግን መጣላቸው የማይቀር ነው። ስንዴው ግን ወደ ጎተራው ይከማቻል። በመጀመርያ ”ንፋስ እንዲሁ ባጋጣሚ ገልጦታል“ ብየ ኣሰብኩ። መጽሓፌንም ድግሜ አስቀመጥኩት። ”መልካም እስኪ ኣሁን ዝም ብየ...“ አሰብኩ። ንፋሱም እየመጣ ሶስት ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ እንዲሁ አደረገ። ”እንግዳ ነገር ነው“ ብየም አሰብኩ።

ከዛም ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ እና “ጌታ ሆይ ይህን መጽሐፍ እንዳነበው ለምን ገለጥክልኝ” ብየ ማሰብ ጀመርኩ። “ እሾህ እና ኩርንችት ግን ብታወጣ፤ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች መጨረሻዋም መቃጠል ነው?” ዙርያየን እየተመለከትኩ አሰብኩት... “ለምን ገልጠህ እንዳነበው አደረግከኝ ብየ ማሰብ ጀመርኩ።”

ወድያውኑም ያለ ምንም ጥርስ ጉተታ ከእግዚኣብሄር የሆነ የጠራ ራእይ ተገለጠልኝ። እግዚኣብሄር ነበረ። አያችሁ? “እነሆ አየሁ፤ ምድር ከፊት ለፊቴ ዞራ አየኋት፤ በደንብ ተዘጋጅታም ነበረች። እነሆም ነጭ የለበሰ ሰው ስንዴ ሲዘራ አየሁት፤ እሱ ዘርቶ በምድር አድማስ በሄደ ጊዜ፤ እነሆ ጥቁር የለበሰ የሚሰቀጥጥ ሰው መጣ በስፍራውም ሁሉ እንክርዳድ መዝራት ጀመረ። አብረው መብቀል በጀመሩ ጊዜ፤ ዝናብ ያስፈልጋቸው ነበርና አብረው ተጠሙ። ሁሉንም ትንንሽየ ራሶቻቸውን ዝቅ ዝቅ በማድረግ ”ጌታ ሆይ ዝናብን ላክ፣ ዝናብን ላክ“ ብለው መጸለይ ጀመሩ። እነሆም ታላቅ ደመና መጣ ዝናብም በሁለቱም ላይ ዘነበ። ዝናብም በዘነበ ጊዜ እነሆ ትንንሾቹ ስንዴዎች በደስታ ”ጌታ ይመስገን! ጌታ ይመስገን“ እያሉ መዝለል ጀመሩ። እነዛ ትንንሽ እንክርዳድም አብረዋቸው በአንድ ስፍራ ሆነው ”ጌታ ይመስገን! ጌታ ይመስገን“ ይሉ ነበር።

ራእዩ ወድያው ተቋረጠ። ዝናብ በጻድቁ እና በሐጥአን እንደሚዘንብ ሁሉ፤ በጉባኤ ላይ በሚወርደው አንድ መንፈስ ግብዞቹም ክርስትያኖቹም አብረው ይደሰቱበታል። በትክክል እንደዛ ነው። እሺ! ምን ማለት ነው? ኣያችሁ? የምትለዩበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው። ብፍሬአቸው ብቻ ነው ልትለዪአቸው የምትችሉት።

ይሄንን ካያችሁ፤ አጃ እና የበረሃ ስንዴ እንዲሁም አንዳንድ ጥራጥሬዎች እውነተኛውን ስንዴ እንደሚመስሉ ሁሉ፤ እነዚህም ምርጦቹን እስኪያታልሉ ድረስ የሚመስል ቅርበት አላቸው። እንደሚመስለኝ ስለ እነዚህ ነገሮች መነገር እና መሰበክ ባለበት ዘመን እየኖርን ነው።

በቁጥር 41 ላይ አስተውሉት፤ ሁለቱም በጣም ስለሚመሳሰሉ፤ በተለይ ደግሞ በመጨረሻ ዘመን መለየት እስከማይችል ድረስ ይመሳሰላሉ... ስለዚ ጌታ እነኚህን ለመለየት በአንድ የሐይማኖት ድርጅት ራሱን አያስጠጋም እነሱን ለይቶ ለማወቅ ሜተዲስት፣ መጥምቃውያን ወይም ጴንጤ ቆስጤ መቀላቀል የለበትም። ነገር ግን እነዚህን ለመለየት መልኣኩን ይልካል። ክፉዎቹን እና መልካሞቹን ለመለየት ከመልአኩ በስተቀር ማንም ኣይችልም። ይሄ ክፉ ነው ይሄንን ደግሞ መልካም ብሎ መለየት የሚችለው እሱ ብቻ ነው። በመጨረሻው ዘመን መላእክቶቹን እንደሚልክ ጌታ ተናግሯልና። አሁኑኑ ወድያው ይልካቸዋል ሳይሆን በመጨረሻው ቀናት ይልካቸዋል ሁሉንም ይሰበስባሉ። ይህ የሚመጣው ጊዜ የመኸር ጊዜ መሆኑን እናውቃለን። መልአክ ማለት “መልእክተኛ” ማለት ነው። ደግሞም ለሰባቱ አብያተ ክርስትያናት የተላኩ ሰባት መላእክት እንዳሉ እናውቃለንና፤ ይሄኛው ግን በቤተክርስያን ዘመናት ውስጥ አይካተትም።

አስቡት ዘሪው ማነው? ዘሩስ ምንድን ነው? አንደኛ ዘሪው ራሱ የጌታ ልጅ ነው። ዘሩንም እየዘራ ሄደ። ከሱ በኋላ ጠላት ዲያብሎስ መጣና የስሕተት ዘር ዘራ። ጓዶኞቼ ከዓለም ጅማሬ እስከ አሁን በእያንዳንዱ ዘመን በዚሁ መልኩ ሲከናወን ነበረ። ከመጀመርያው ጀምሮ በዚ ተመሳሳይ አካሄድ ነበረ የጀመረው።

----
ሁላችንም እንደምናውቀው በዘፍጥረት 1 ላይ የተቃዋሚ ዘር ሲዘራ የተገኘውን “ዲያብሎስ” ተብሎ ተሰይሞአል። እንደገናም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13፤ ኢየሱስ፥ የትኛውም ከቃሉ የተለየ ሁሉ “ዲያብሎስ ” በማለት ሰይሞታል። እንዲሁም በዚሁ 1965 ዓ/ም በተጻፈው በእግዚኣብሄር ቃል ላይ ሌላ የተቃረነ ከቃሉ የተለየ ዘር የሚዘራ እና ትርጉም የሚሰጥ ሁሉ ከስሕተት ዘር ነው። እግዚኣብሄር አይቀበለውም። አይቀበለውም። እንደሰናፍጭ ዘር ከማንም ጋር አይቀላቀልም። በርግጥ አይቀላቀልም። ዋናው መሆን አለበት። የጥፋት ዘር!

እግዚአብሄር ዘሩን በኤደን ገነት በዘራ ጊዜ ኣቤልን እንዳገኘ እንመለከታለን። ነገር ግን ደግሞ ሰይጣን የስሕተት ዘሩን በዘራ ጊዜ ቃየንን አገኘ። አንደኛው ጻዲቅ ዘር፥ ሌላኛው ደግሞ ክፉ ዘር አፈሩ። ያኔ ሄዋን የእግዚኣብሄርን ቃል ለሚቃወመውን የስሕተት ዘር ጆሮዋን ከሰጠች ጊዜ ጀምሮ የሐጢአትን ኳስ መንከባለል ጀመረ፤ እስከ አሁንም ድረስ እየቀጠለ ይገኛል። መላእክቶቹ መጥተው እስኪለያዩአቸው ድረስ፤ እግዚአብሄር ልጆቹን ወደ መንግስቱ እስኪ ወስዳቸው ድረስ፤ እንክርዳዱም ወደ መቃጠል እስኪገባ ድረስ፤ ልንለያቸው ፍጹም ያስቸግረናል። እነዛን ሁለት ግንዶችን አስታውሱ።

ዛሬ እያጠናናት ባለችው በዚች ትንሿ ጽሁፍ እግዚአብሄር “አብረው ይደጉ” ብሎ እንደተናገረ፤ እነዚ ሁለት ዘሮች አብረው አደጉ። ስለዚህ ቃየን ሚስቱን ይዞ ወደ ኖድ ምድር ሲሄድ ኣቤል ታረደ እግዚኣብሄርም በሱ ምትክ ሴትን አስነሳ። ከዛም ጊዜ ጀምሮ የእውነት እና የስህተት ትውልድ መቆጠር ጀመረ። ከጊዜ በኋላ ግን እነዚህ ዘሮች መቀላቀል ጀመሩ፤ እግዚአብሄርም... እግዚአብሄር እስኪያጠፋቸው ድረስ ክፉ ሆኑ።

በመጨረሻም የሁለቱም ዘሮች ራሶች ማለት የተቃዋሚው ዘር እና የእግዚኣብሄር ዘር እስኪገለጡ ድረስ ተጓዙ። የሁለቱም መቆሳሰል በአስቆርቱ ይሁዳ እና በክርስቶስ እየሱስ መካከል ነበረ። ኢየሱስ የእግዚአብሄር ዘር፤ የእግዚአብሄር የፍጥረቱ መጀመርያ ሆኖ ከእግዚኣብሄር የሚያንስበት ምንም ነገር አልነበረም። አስቆርታዊ ይሁዳም ከጥልቅ መጥቶ ወደ ጥልቅ የተመለሰ የጥፋት ልጅ ነበረ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሄር ልጅ ነበረ፤ የእግዚኣብሄር ቃል የተገለጠው ቃል ነበረ። ኣስቆርታዊ ይሁዳም እንደ ጥፋት ዘርነቱ የዲያብያሎስ ዘር ሆኖ ለማታለል ወደ ዐለም መጣ። ከመጀመርያ እንደ ቃየን እንደ አባቱ ነበረ።

ይሁዳ የድርጅት የቸርች ሰው ነው። ከልቡ አማኝ አልነበረም፤ እምነትም አልነበረውም (ኢየሱስን ባልካደ ነበርና።) እዩት፡ ከዐለም ብልጭልጭ ጋር እና ከኢየሱስ ጋር ጓደኛ ለመሆን ያንን የስሕተት ዘሩን ሲዘራ እዩት። ነገር ግን ይሄንን ሁሉ ለማከናወን ጊዜው ረፈደበት። በእንጥፍጣፊ ሰዓታት ውስጥ ይሄንን ሰይጣናዊ ስራ ባደረገ ጊዜ ወደ ፊትም ወደ ኋላም የማይባል መስመርን ረገጠ። በአታላይነቱ መቀጠል ስለነበረበት ያ ተቃዋሚው የስሕተት ዘሩን ዘራ። በዘመኑ ከነበሩ ታላላቅ ድርጅቶች፣ ከፈሪሳውያን እና ሶዱቃውያን ሙገሳን ፈለገ፤ ገንዘብን በማጠራቀም በህዝቡ መካከል መታወቅን ቋመጠ። ብዙ ሰዎች በሰዎች ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ብለው በተቃዋሚው ዘር ይጠመዳሉ። ከሰው መገስ ለማግኘት ከማሰብ ይልቅ ከእግዚኣብሄር እንፈልግ። ይሁዳም ተቃዋሚው የስሕተት ዘር በገባበት ወቅት፤ ያደረገው ይህንኑ ነው።

ሁላችንም እንደምናውቀው ኢየሱስ ቃል ነው። ዮሃንስ 1 ላይ “በመጀመርያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚኣብሄር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ። ቃል ስጋ ሆነ በእኛም አደረ። ስለዚ ቃሉ ዘር ነው፤ ዘሩም ስጋ በመሆን በእኛ ኣደረ።

ስለዚ ይሁዳ የጠላት ዘር የሆነውን ተቃዋሚ ዘር ከሆነ ፤ እንግድያውስ እሱም የአስቆርቱ ይሁዳ በሚባል አካል ስጋ በመሆን በእኛ አደረ ማለት ነዋ። እሱ እምነት ያልነበረው ሰው ነበር፤ ምናልባት እንዲሁ እምነት የሚመስል እምነት አስመሳይ እምነት እንዳለ ሁሉ፤ ለእሱ እምነት ብሎ የሚለው የእራሱ እምነት ነበረው። እውነተኛው የእግዚአብሄር እምነት እግዚአብሄር ያምናል። እግዚአብሄርም ራሱ ቃል ነው በሱ ላይም ምንም ነገር አይጨመርበትም። የእግዚአብሄር ቃል፤ ትንሽ ብንጨምር ወይም ብናጎድል እድል ፈንታችን ከሕይወት መጽሐፍ እንደሚወሰድብን ይናገራል። በራእይ መጽሓፍ በመጨረሻው መዕራፍ 22 ላይ።

ከጥንቷ ከመጀመርያዋ መጽሓፍ ቅዱስ ጀምሮ እግዚአብሄር አንድም ቃል እንዳይተላለፉ ተናገራቸው “ቃል ሁሉ መጠበቅ አለበት” በዛም ቃል ደግሞ መኖር ይጠበቅባቸው ነበረ። በመጽሓፉ መካከል ኢየሱስ መጣና “ሰው በእግዚአብሄር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” ብሎ ተናገረን። አሁንም በራእይ በመጨረሻው ዘመን “ከመጽሓፉ ማንም አንዳች ቃል ቢያጎድል ወይም ቢጨምር እድል ፈንታውን ከሕይወት መጽሓፍ ይጎድልበታል ይለናል።”

ስለዚ ከዚ ሌላ ጥላ አይኖርም፣ ያልተሸቃቀጠው እውነተኛው የእግዚአብሄር ቃል! እነሱም የእግዚኣብሄር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች በወንድ ፈቃድ፣ በእጅ ሰላምታ ወይ ደግሞ በተለየ የጥምቀት ስርዓት ያልተወለዱ፣ ነገር ግን ከእግዚኣብሄር መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ተወልደው ቃሉ በህይወታቸው የሚያፈራባቸው ናቸው። እውነተኞቹ የእግዚኣብሄር ዘር!

ጠላት ቤተክርስትያን ውስጥ በመግባት ራሱን በህግ እና በስርዓት ፍጹም ያደርጋል። ነገር ግን አይደለም ... ከእውነተኛው ከእግዚኣብሄር ቃል ለመጋጨት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ ሁሉ የተቃዋሚው የተሳሳተ ዘር ነው። ታድያ እንዴት እናውቃለን? እንደሚባለው “እሺ! እነሱ፣ ቃሉን ለመተርጎም መብት አለህን?” ፈጽሞ፡ የለህም! የእግዚአብሄርን ቃል ለመተርጎም ማንም ሰው መብት የለዉም። ቃሉን የሚፈታው እራሱ ለራሱ ነው። አደርጋለው ብሎ የሰጠውን ቃል እራሱ ያደርገዋል፣ አፈታቱም እንዲሁ ነው። ከእግዚኣብሄር ቃል ውጪ የሆነ ተቃዋሚ ሁሉ ስሕተት ነው። ሙሉ በሙሉ።

እናም እንዳልኳችሁ ይሁዳ እምነት የሌለው ሰው ነው። የአስመሳይነት እምነት ነበረው። የእግዚኣብሄር ልጅ እንደሆነ የሚያምንበት አስመሳይ እምነት ነበረው። እሱ የእግዚአብሄር ልጅ ሊሆን ይችላል የሚልበት እ - እ እምነት ነበረው፤ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን ግን አያውቀውም ነበረ። ባላደረገውም ነበረ። በእውነተኛው የእግዚኣብሄር ቃል ላይ የሚያመቻምች ሰው ሁሉ አስመሳይ አማኝ ነው። ትክክለኛው የእግዚአብሄር አገልጋይ ከቃሉ ጋራ ይጣበቃል።

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ... የስህተት ዘር።


የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

ሰባት ማኅተሞች
ተከታታይ።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤

እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው።

ወደ ዕብራውያን 6:7-8


ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet.

(PDF እንግሊዝኛ)

ጋብቻ እና ፍቺ።

(PDF)

William Branham
Life Story.

(PDF እንግሊዝኛ)

How the Angel came
to me.

(PDF እንግሊዝኛ) 


መልዕክት ሃብ... ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።