የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት።


  የራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።

የሥላሴ ስህተት።


William Branham.

የዮሐንስ ራእይ 1:5,
ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥

የዮሐንስ ራእይ 1:8,
ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።

አሁን እነዚህ ሁሉመገለጫዎች “ያለ,” እና “የነበረ,”እና “የሚመጣ,” እና “የታመነ ምስክር” እና “ከሙታንም በኩር,” እና “የምድርም ነገስታት ገዥከሆነ,” እና “አልፋና ዖሜጋ,” እና “ሁሉን ቻይ,”እነዚህ ሁሉመገለጫዎች የአንዱ እና የአንዱ አካል የሆነዉ ሀጥያታችንን ሁሉበገዛ ደሙ ያጠበን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስያሜዎች እና መገለጫዎች ናቸዉ፡፡

በዮሃንስ ላይ የነበረዉየእግዚአብሔር መንፈስ በዚህ መልኩ የገለጸበት ምክንያት ከሁሉ በላይ የሆነዉን የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮትነት እና የሙላተመለኮት አንድ አምላክነትን ለመግለጥ ነዉ፡፡ ዛሬ ዛሬ ከአንድ በላይ ሶስት አምላክ አለ የሚል የጅምላ ስህተት አለይሄ መገለጥለዮሃንስ በራሱ በኢየሱስ አማካኝነት ሲሰጠዉ ይሄንን ስህተት ያስተካክለዋል ሶስት አማላክ ሳይሆነ በሶስት የተለያዩ ተግባራትየተገለጠ አንድ አምላክ ነዉ አብ፤ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በሚል ስያሜ ያለ አንድ አምላክ አለ፡፡ የቀድሞዋ ቤተክርስቲያንየነበራት መገለጥ ይሄ ነበር ስለሆነም አሁን ባለንበት ዘመንም ከትክክለኛዉ የዉሃ አጠማመቅ ቀመር ጋር ተያይዞ መቃናትአለበት፡፡

አሁን አሁን ዘመናዊየስነመለኮት አጥኚዎች በታዋቂ የክርስቲያን መጽሄቶች ላይ እንደተጻፈዉ ከእኔ ጋር አይስማሙም የስላሴ አስተምህሮት በዋናነት በብሉይኪዳን እንደተገለጸ ሁሉ በግልጽ ሁኔታ በአዲስ ኪዳን ዋና አስተምህሮት ላይም እናገኘዋለን፡፡ ከአንድ በላይ አምላክ በሚለዉጉዳይ ላይም የአዲስ ኪዳን መጽሃፍ ከብሉይኪዳን መጽሃፍ ላይ ከተገለጠዉ በላይ በደንብ ይቃወማል ፡፡

ሆኖም ግን አዲስ ኪዳን ላይ እኩል ግልጽ በሆነ መልኩ አብ አምላክ እንደሆነ ፤ ልጅአምላክ እንደሆነ፤ መንፈስ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ ያስተምራል እናም እነዚህ ሶስቱ የአንድ አካል መገለጫዎች ሳይሆኑ አንዳቸዉ ከሌላኛዉ ጋር በእዉነተኛ ዝምድና ዉስጥ የቆሙ ሶስት ራሳቹዉን የቻሉ አካሎች ናቸዉበሚል አስተሳሰብ ደግሞ በሶስት አካል ዉስጥ የሚኖር አንድ አምላክ የሚል የታወቀ አስተምህሮት አለ፡ የስላሴ አስተምህሮት ታላቁሚስጥርም በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለዉ አምላክ በሶስት አካል ዉስጥ የሚኖር አንድ አምላክ መሆኑ ነዉ ይላሉ፡፡ በርግጥ ሶስት አካል ያለዉ አንድ አምላክ እንዴት ሊኖርይችላል?በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥእንዲህ አይነት አስተምህሮት የሚደግፍ ነገር አለመገኘቱ ብቻ ሳይሆን በአእምሮ እንኳን ምክንያታዊነት የጎደለዉ አስተሳሰብእንደሆነ ያሳያል ሶስት የተለያዩ አካላት፤ ተመሳሳይ ማንነት ያላቸዉ ሶስት አማልክት ይሆናሉ እንጂ ቋንቋ ትርጉሙን ካላጣበስተቀር አንድ አምላክ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

አስኪ እነዚህን ቃላቶችበደንብ አድምጧቸዉ “አልፋ እና ኦሜጋ፤ መጀመሪያ እና መጨረሻ፤ ያለ፤የነበረ ፤የሚመጣ ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ፡፡”ይህ አምላክ ነዉ፡፡ አንድነብይ የሆነ ሰዉ ብቻ የተናገረዉ አይደለም ይህ አምላክ ነዉ፡፡ የሶስት አምላኮች መገለጥም ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነዉ የአንድ አምላክ መገለጥ ነዉ፡፡

በመጀመሬይቷ ቤተክርስቲያን በሶስት አምላክ አልነበረም የሚያምኑት በሐዋሪያቱ መካከል እንዲህ ያለ እምነት ያለዉ አታገኙም እንዲህ ያለዉ አስተምህሮት እና ስጋዊ የሆነ አስተሳሰብ የተነሳዉ ሐዋርያቱ ካለፉ በኋላኒቂያ ተብሎ ከሚታወቀዉ ጉባዔ ጀምሮ ነዉ፡፡ የሙላተ መለኮት አስተምህሮት በኒቂያ ጉባዔ ሁለትየተለያዩ ጽንፍ የያዙ ሃሳቦችን አስነሳ አንደኛዉ በብዙ አምላክነት የሚያምን ጽንፍ በሶስት አምላክ የማመን ጽንፍ ሲሆን ሌላኛዉአንድ አምላካዊነት ነዉ ነገር ግን ለዮሃንስ በመንፈስ አማካኝነት ለቤተክርስቲያን የመጣዉ መገለጥ “እኔ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስሁሉ በሁሉ የሆንኩ ነኝ ሌላ አምላክ የለም የሚል ነዉ፡፡”ማህተሙንም በዚህ መገለጥ ላይ አደረገዉ፡፡

አስኪ ይሄን ነገር ከግምት ዉስጥ አስገቡት የኢየሱስ አባት ማን ነበር? ማቴ፡1፡18 “ከመንፈስ ቅዱስ ጸንሳተገኘች” ይላል ኢየሱስ እራሱ ደግሞአግዚአብሄር አባቱ እንደሆነ ይናገራል እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ከሄድን እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔርመንፈስ ቅዱስ አንድ መንፈስ እንደሆነ ያሳያል በርግጥም ልክ ነዉ ካልሆነ ግን ኢየሱስ ሁላት አባቶች አሉት ልንል ነዉ በሌላቦታ ደግሞ አስተዉሉ ኢየሱስ እኔ እና አብ አንድ ነን ይላል ሁለት አይደለም አንድ ይሄም አንድ አምላክ እንደሆነ ያሳያል፡፡

ይሄ ጉዳይ በታሪክም ሆነ በመጽሃፍ ቅዱስ እዉነት ቢሆንም ሰዎች ሶስት የሚባለዉ ነገርከየት እንደመጣ ይደነቃሉ ክርስቶስ ከሞተ በኋላ በ325 አመት የኒቂያ ጉባዔ ከተካሄደ ጀምሮ ነበር መሰረተ እምነት ሆኖየተጀመረዉ ይህ ስላሴ (በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ፈጽሞ የማይገኝ ቃል) የሮማዊያንን ብዙ አማልክት መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡ሮማዊያን ጸሎት የሚጸልዩላቸዉ ብዙ አማልክት ነበራቸዉ፡፡

ለቅድሚያ አያቶቻቸዉም እንደአማላጅ እንዲሆኑላቸዉ ወደእነሱ ይጸልያሉ፡፡ ለአማልክቶቻቸዉ አዲስ ስም የመስጠት ጅማሬ መሆኑ ነዉ፡፡ የበለጠ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ደግሞ የቅዱሳንምስም አለበት ጁፒተር፤ቬኑስ፤ማርስ በማለት ፈንታ ጳዉሎስ፤ጴጥሮስ፤ፋጢማ፤ክርስቶፎር … የመሳሰሉትን ስያሜዎች ይጠቀማሉ የጣኦታዊነትአምልኳቸዉ አንድ አምላክ በሚል ብቻ ሊሰራላቸዉ ስላልቻለ ለሶስት ከፋፈሉት ልክ እንደ ቅድመ አያቶቻቸዉ የቅዱሳን አማላጅነትን እንዲሆን አደረጉ ከዛ ጊዜ አንስቶም ሰዎች በሶስት መልኩ የተገለጠ አንድ አምላክ ብቻመሆኑን ማስተዋል አቃታቸዉ፡፡

እንደመጽሃፍ ቅዱስ አንድአምላክ ብቻ እንዳለ ያዉቃሉ ነገር ግን አስደናቂ የሆነ አስተምህሮት ለማስመሰል እግዚአብሔር በአንድ የወይን ዘለላ ወይም ጭብጥዉስጥ እንዳለ በእኩል መለኮትነት ያለ ሶስት አካል ያለዉ አምላክ ነዉ ይላሉ ፡፡ ነገር ግን ራእይ ላይ በግልጽ እንደሚናገረዉኢየሱስ ያለ፤የነበረ፤ የሚመጣ እሱ አልፋ እና ኦሜጋ ነዉ ይላል ማለትም ከ ሀ እስከ ፐ ሁሉ በሁሉ ነዉ ማለት ነዉ እሱ ሁሉንቻይ የሆነ ሁሉ በሁሉ የሆነ አምላክ ነዉ፡፡ እሱ የሳሎን ጽጌሬዳ፤ የቆላአበባ፤የንጋት ኮከብ፤ የጽድቅ ዛፍ፤ አባት፤ ልጅ እናመንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡ እርሱ አምላክ ነዉ፡፡ ሁሉንቻይ የሆነ አምላክ አንድ አምላክ ነዉ፡፡

1ኛጢሞቲዮስ 3፡16 እንዲህ ይላል “እግዚአብሔርን የመምሰልሚሲጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነዉ፤ በሥጋ የተገለጠ፤ በመንፈስ የጸደቀ፤ ለመላእክት የታየ፤ በአህዛብ የተሰበከ በአለም የታመነበክብር ያረገ” መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረዉ ይሄን ነዉ እዚህ ላይ አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ አካል ብሎአይናገርም፡፡ የሚለዉ እግዚአብሔር በስጋ የተገለጠ አንድ አምላክ መሆኑን ነዉ ያ ሁሉን ነገር ይደመድመዋል አምላክ እራሱስጋንለብሶ መጣ ይሄ ሌላ አካል ያለዉ አምላክ አያሰኘዉም እራሱ አምላክ ነዉ ስለዚህ ይሄ ያኔም የመገለጥ ጉዳይ ነዉ አሁንምየመገለጥ ጉዳይ ነዉ አንድ አምላክ፡፡

ወደ መጽሃፍ ቅዱስእንመለስና ከጅማሬዉ ስለራሱ በገለጠበት መልኩ እንየዉ ታላቁ ያህዌበእሳት አምድ ምሳሌ እንደ ቃል ኪዳን መላእክ በእሳት አምድ ዉስጥ በመኖር እና የእስራኤልንህዝብ እለት እለት በመምራት ተገለጠ፡፡ በቤተመቅደስ መምጣቱን በታላቅ ደመና በመታየት አሳወቀ፡፡ አንድ ቀን ግን ከድንግል በተወለደ በተዘጋጀለት አካል ተገለጠእስራኤላዊያን ካዘጋጁለት የቤተመቅደስ ድንኳን በላይ የሆነዉ አምላክአ ሁን በሰዎች መካከል እራሱን በሰዉ ስጋበተሰራ ቤተመቅደስ አኑሮ ተመላለሰ፡፡ ነገር ግን ያ እራሱ አምላክ ነበር፡፡

መጽሃፍቅዱስ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዉስጥ እንዳለያስተምራል አካሉ ኢየሱስ ነዉ በአካሉም የእግዚአብሔር ሙላት ነበረበት ከዚ ሌላ ግልጽ የሆነ ነገርየለም ሚስጥር ነዉ አዎነገር ግን እዉነታዉም ይህ ነዉ ስለዚህ ቀድሞም ሶስት አካል አልነበረም አሁንም ያዉ ነዉ ተመሳሳይ አንድ አምላክ እናም ይሄዉአንዱ አምላክ በስጋ ተገለጠ፡፡

ኢየሱስ እንዲህ አለ “ከእግዚአብሔር ወጥቻለሁ ወደ እግዚአብሔርም እመለሳለሁ” ዮሀንስ 16፡7-28 ያነዉ በትክክል የተከናወነዉ፡፡ በሞት፤ በመቀበር፤ ከሞት በመነሳት እና በማረግ መልክ ከምድር የነበረዉን ቆይታ ተወገደ ጳዉሎስበደማስቆ መንገድ ላይአገኝዉና ኢየሱስ ለጳዉሎስ እንዲህ አለዉ “ሳኦል ሳኦል ሆይ ስለምን ታሳድደኛለህ?” ጳዉሎስም መልሶ “ጌታ ሆይ አንተ ማን ነህ?” ሲለዉ “እኔ ኢየሱስ ነኝ” ብሎ መለሰለት እርሱየሚያሳዉር የእሳት አምድ ነበር፡

ተመልሼ እመጣለሁ እንዳለ እንዳዛዉ አደረገ በዚህ የስጋ ቤተመቅደስ በሰዉ አካል ከመገለጡ አስቀድሞ ወደነበረበት ማንነት ተመለሰ ያን ነበር ዮሀንስ የተመለከተዉ ዮሃንስ 1፡18 “እግዚአብሔርን ያየ አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍያለዉ አንድያ ልጁ ተረከዉ እንጂ” እዚህ ጋር አስተዉሉ ዮሀንስ ኢየሱስ ብሎ ሲናገር በአባቱ እቅፍ ያለዉን ኢየሱስን ነዉ፡፡

ሉቃ 2፡11 እንዲህ ይላል “አነሆ በዳዊት ከተማ አዳኝ የሆነዉ ክርስቶስ ጌታተወልዶላችኋልና”ክርስቶስ ሆኖ ተወለደ ከስምንት ቀናት በኃላም በሚገረዝበት ቀን ኢየሱስ የሚል ስም ተሰጠዉልክ መልአኩ እንደተናገረዉ እኔ ብራንሃም ሆኜ ተወልጃለሁ የተወለድኩ ቀን ደግሞ ዊልያም የሚል ስም ተሰጠኝ እርሱ ክርስቶስነበር በሰዎች መካከል ሲወርድ ግን ስም ተሰጠዉ ያ የተገለጠዉ የሚታየዉ የሰዉ ቤተ መቅደስ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ፡፡ እርሱ የክብር ጌታ ነዉ፤በስጋ የተገለጠ ሁሉን ቻይ ነዉ፤እርሱእግዚአብሔር አባት፤ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡ እርሱ ሁሉንም ነዉ፡፡

ውስጥ ሙሉ መለያ ያንብቡ... የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ።

የውርድ(እንግሊዝኛ)።   Godhead Explainedየራዕይ መጽሐፍ ተከታታይ።
በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይቀጥላል።
(የፍጥሞ ራዕይ።)


የክርስቶስ ምሥጢር
ተከታታይ።

የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ድረ።

እግዚአብሔር እና ሳይንስ
ተከታታይ ኢንዴክስ።

በራእይ መጽሐፍ ላይ።

 

ጥሩ ዜናው።
ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ሞቷል።

የውኃ ጥምቀት።
መንገዱ ይህ ነው.
በእርሱ ሂድ.

የመለኮት ገልጿል።

 

መልእክት ዋና ዋና ትምህርቶች።

ከተፈጥሮ በላይ ደመና።

የእሳት ዓምድ።

መቃብሩ ባዶ ነው።
እርሱ ሕያው ነው።

አርኪኦሎጂ።
ሰዶምና ገሞራ።

የመኖር ቃል ተከታታይ።

 

የእሳት ዓምድ።
የመለኮት አብራርቷል።

የማብቂያ ጊዜ ተከታታይ።

 

የኖህ መርከብ።

ወቅታዊ ምርምር።
ጋብቻ እና ፍቺ።
ክርስቲያን የእግር ጉዞ
ተከታታይ። - ምልክት።

ሚቶሎጂ። ባቢሎን የምንጭ።

የመጀመሪያው ኃጢአት።
አንድ አፕል ማለት ነው?።

በለዓም መሠረተ ትምህርት ነው።

እንደሆነ ሴት ኤልዛቤልን።

የእኛ ዕድሜ በሎዶቅያ።

 
 

የእሱ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ክርስቶስ ነው።

የኒቆላውያንን ትምህርተ።

የፍጥሞ ራዕይ።

 

ሚስጥራዊ ባቢሎን።

ሰባት ማኅተሞች
ተከታታይ።

የመልእክታችን ዝርዝር።

የገና ተከታታይ።

  ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል...

እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤

ኦሪት ዘዳግም 6:4


ኢየሱስ ክርስቶስ
አምላክ ነው።
የብሉይ ኪዳን
ይሖዋ እሱ የአዲስ
ኪዳን ኢየሱስ
ነው።


ሙሉ መጠን ሥዕሎች ወይም ፒዲኤፍ ለማውረድ ምስል ላይ ጠቅ ያድርጉ።


Acts of the Prophet.

(PDF እንግሊዝኛ)

The Two Babylons

by Rev Alexander Hislop.
(PDF እንግሊዝኛ)

ቻይና ውስጥ በረዶ ውስጥ
አንዲት ተራራ እና
የጽጌረዳን።

የእሳት በአበቦች።

የእሳት ዓምድ
- የሂዩስተን 1950።

አንድ ፒራሚድ ዓለት
ላይ ብርሃን ነው።


መልዕክት ሃብ...ቋንቋዎን ይምረጡ. ወንድም ብራናም ነፃ መልዕክቶችን የውርድ።